የሰብዓዊ መብት ይዞታ በኦሮሚያ | ኢትዮጵያ | DW | 23.02.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የሰብዓዊ መብት ይዞታ በኦሮሚያ

በኒው ዮርክ የሚገኘዉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት «ሂውመን ራይትስ ዎች» ይፋ ባዳረገዉ ዘገባ በኦሮሚያ ላለፉት አራት ወራት እየተካሄደ ያለዉ ተቃዉሞ መቀጠሉን አስታዉቋል። በዚህ ተቃዉሞ የኢትዮጵያ መንግሥት በመቶዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎችን መግደሉንና በሺዎች የሚቆጠሩትን ማሰሩን በዘገባዉ አስነብቦአል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:04

ኦሮሚያ

ላለፉት አራት ወራቶች በኦሮሚያ ክልል እየተደረገ ያለዉን ተቃዉሞ አሰመልክቶ የኢትዮጵያ መንግሥት የፀጥታ ኃይል በወሰደዉ ርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎችን መግደላቸዉንና በሺዎች የሚቆጠሩ መታሰራቸዉን የተለያዩ ዘገባዎች ያሳያሉ። ይሁን እንጂ በኒው ዮርክ የሚገኘዉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት «ሂውመን ራይትስ ዎች» የኢትዮጵያ መንግስት በኦሮሚያ ክልል እያካሄደ ያለዉ ርምጃ በፖሊስ ደረጃ ያወጣዉና ተግባራዊ በማድረግ ላይ ያለዉ ጉዳይ መሆኑን ሰኞ ጥዋት ይፋ ባዳረገዉ ዘገባ ጠቅሶዋል። ይህኑ ፖሊሲ በተመለከተ «ሂውመን ራይትስ ዎች» አንድ የኢትዮጵያ መንግሥት ደሕንነት አባልን ዋቢ በማድረግ አሳይቶአል። በዘገባዉ መሰረት መንግሥት ታዋቂ የሆኑ የኦሮሞ ተወላጆችን፣ ማለት ፖለቲከኞችን፣ ተማሪዎችንና ከያንያን ለማጥቃት ፖሊሲ ይዞአል። ለምሳሌ በቅርብ ግዜ የታሰሩት አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎች ማኅበረሰቡን ማደራጀት የሚችሉ ግለሰቦች እንደሆኑ በዘገባዉ ተመልክቶአል።
ወደ 60 የሚጠጉ ሰዎችን አነጋግረናል የሚለዉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዉ ድርጅት «ሂውመን ራይትስ ዎች» አገሪቱ ዉስጥ በደህንነት ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ሰዎችን ማነጋገራቸዉን በተቋሙ የአፍሪቃ ቀንድ ተመራማሪ ፌልክስ ሆርን ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። ይህን ፖሊስ አስመልክቶ የመረጃዉን ታዓማኒነት ሆርን ሲጠየቁ፣

«እሄ ትክክለኛ መረጃ ነዉ። ምክንያቱም በዚህ ተቃዉሞ የመንግስት ስትራቴጂ ታዋቂ ኦሮሞ ሰዎችን ማሰር መሆኑ ግልፅ ነበር። ብዙዎቹ በቀጥታ በዚህ ተቀዉሞ አልተሳተፉም። እናም እነሱን ማሰር ትርጉም የለዉም። ግን ብዙ ቁጥር ያላቸዉ ኦሮሞ ከያኒያን፣ የተቀዋሚ ፓርቲዉ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ በቀለ ገርባ እናም ሌሎችን ጨምሮ ታስረዋል። በቀለ ገርባ የሚታወቀዉ በሰላማዊ ትግል አራማጅነት ነዉ። እነዚህን ሰዎች ማሰር ለመንግሥት ነገሮችን ለመረጋጋት መስሎት ይሆናል፣ ግን እየተካሄደ ያለዉ እዉነታ ይህ ነዉ።»


ይሁን እንጅ፣ ይላሉ ፊሊክስ ሆርን፣ መንግሥት እየወሰደ ያለዉ ርምጃ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነዉ። ምክንያቱም ርምጃዉ ነገሮችን ከማቀዝቀዝ ይልቅ እያባባሰ መሆኑን ፊሊክስ ሆርን ተናግረዋል። ነገሮችንም ለማረጋጋት ከመንግሥት ጋርም ለመግባባት በኦሮሞ ሰዎች በኩል ማንም የለም ያሉት ሆርን፣ ምክንያቱ ደግሞ ከህዝብ ጋር ተነጋግሮ ነገሮችን ለማብረድ የሚችሉት ሰዎች እስር ላይ ነዉ የሚገኙት ሲሉ ተናግረዋል።
ግን የኢትዮጲያ መንግስት ይህን ፖሊስ ይዞ ከቀጠለበት ምን ልመጣ ይችላል ተብሎ ስጠየቁ ሆርኔ መልሳቸዉ እንዲህ ነበር፣
«ምን ሊያመጣ ይችላል ብሎ አሁን መተንበይ ይከብዳል። ግን፣ ግልፅ ይሆነዉ ነገር በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የነበሩት አብዛኞቹ ልጆች ሲሆኑ፣ የመሳሪያ ርምጃ በነሱ ላይ መዉሰድ መንግስት ላይ ያላቸዉን ብሶት ያባብሳል እንጅ አያረጋጋም። አብዛኞቹ ያነጋገርናቸዉ ወጣቶች፣ ትምህርት ቤት የሚሄዱት ስለወደፊት ተስፋቸዉ አስበዉ ቢሆንም፣ ከሳምንት በኋላ መተስር፣ መመታት፣ ከአገር መሰደዱ ከመንግሥት ጋር ያለቸዉን ብሶት እያባባሰ ይገኛል። ይህን ለማረጋጋት ለመንግስትም ወደፊት ካባድ እየሆነ ነዉ። መንግሥት ማድረግ ያለበት ግጭቱን ማስቆም፣ አለግባብ ኃይል ተጠቅሞዋል የተባሉትን የደኅንነት ሰዎች ለፍርድ ማቅረብ እና ከኦሮሞ ኅብረተሰብ ጋር ቁጭ ብሎ ስላለዉ ብሶት መወያየት ነዉ።»
እስካሁን የመንግሥት ታጣቂ ኃይሎች በወሰዱት ርምጃ ይላል ዘገባዉ በተቀዋሚዎች ላይ ሆን ብሎ መተከስ፣ ተማሪዎችን ለሞት እንደዳረጋቸዉና፤ እስር ቤት የገቡት ደግሞ ለእንግልትና ስቃይ ማደረጋቸዉን ያሳያል። አብዛኞቹ ታሳሪዎች የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አባል ናችሁ፤ አልያም ደግሞ በአደባባዩ ተቃዉሞ ጀርባ ያለዉን ኃይል አዉጡ በመባል ይገረፋሉ፤ ሲል ዘገባዉ ያትታል።
መርጋ ዮናስ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic