የሰባት የኢትዮጵያተ ቃዋሚ ፓርቲዎች መግለጫ  | ኢትዮጵያ | DW | 25.07.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የሰባት የኢትዮጵያተ ቃዋሚ ፓርቲዎች መግለጫ 

ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ከሰኔ 15፣2011 ዱ ግድያ በኋላ እየተፈጸመ ነው ያሉት የጅምላ እሥራት ማስፈራራት በአስቸኳይ እንዲቆም ጠይቀዋል።በአማራ ክልል የታሰሩ ንጹሀን ያሏቸው ዜጎች ጉዳያቸው ተጣርቶ ከእስር እንዲለቀቁም አሳስበዋል።የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት ባልደራስ አባላት እና ደጋፊዎች ላይ ደረሰ ያሉት መዋከብ እንዲቆምም ጥሪ አቅርበዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:23

የሰባት ተቃዋሚ ፓርቲዎች መግለጫ


ተቃዋሚውን የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድን ጨምሮ ግንባር ለመፍጠር በሂደት ላይ ያሉ 7 ተቃዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ መግለጫ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ሰጥተዋል። ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ከሰኔ 15፣2011 ዱ ግድያ በኋላ እየተፈጸመ ነው ያሉት የጅምላ እሥራት ማስፈራራት በአስቸኳይ እንዲቆም ጠይቀዋል።በአማራ ክልል የታሰሩ ንጹሀን ያሏቸው ዜጎች ጉዳያቸው ተጣርቶ ከእስር እንዲለቀቁም አሳስበዋል።የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት ባልደራስ አባላት እና ደጋፊዎች ላይ ደረሰ ያሉት መዋከብ እንዲቆምም ጥሪ አቅርበዋል።መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል።     
 

Audios and videos on the topic