የሰበታ ተፈናቃዮች ምሬት  | ኢትዮጵያ | DW | 18.03.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

    የሰበታ ተፈናቃዮች ምሬት 

እነዚሁ ከ4 ወር በፊት ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰዎች ከ3 ሺህ በላይ መሆናቸውን በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ ጽህፈት ቤት በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል። ቤታቸው በመፍረሱ በአብያተ ክርስቲያን ተጠልለው እንደሚገኙ የተናገሩት እነዚሁ ሰዎች የሚበሉት እና የሚጠጡት እንደሌላቸው የልጆቻቸውም ትምሕርት መስተጓጓሉን በምሬት ገልጸዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:17

«ቤት የፈረሰባቸው ሰዎች ከ3 ሺህ በላይ ይሆናሉ»

ሰበታ ውስጥ ወለቴ ቀበሌ 03 ይገኙ የነበሩ መኖሪያ ቤቶቻቸው ህገ ወጥ ተብሎ በመፍረሱ ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎች ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን አስታወቁ። እነዚሁ ከ4 ወር በፊት ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰዎች ከ3 ሺህ በላይ መሆናቸውን በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ ጽህፈት ቤት በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል። ቤታቸው በመፍረሱ በአብያተ ክርስቲያን ተጠልለው እንደሚገኙ የተናገሩት እነዚሁ ሰዎች የሚበሉት እና የሚጠጡት እንደሌላቸው የልጆቻቸውም ትምሕርት መስተጓጓሉን በምሬት ገልጸዋል። መንግሥት እኛን ህገ ወጥ እያለ በህገ ወጥ መንገድ ሊያስተናግደን አይገባም የሚሉት እነዚሁ ተፈናቃዮች አፋጣኝ መፍትሄ እንዲፈለግላቸው ጠይቀዋል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ 

Audios and videos on the topic