የሰርቢያ ና የኮሶቮ ውዝግብ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 02.08.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የሰርቢያ ና የኮሶቮ ውዝግብ

የቀድሞዋ የሰርብ ግዛት ኮሶቮ ነፃነትዋን ካወጀች 3 ዓመታት ቢያልፉም ከጎረቤትዋ ከሰርቢያ ጋር መልካም ግንኙነት መፍጠሩ ግን አሁንም አዳጋች ሆኖ እንደዘለቀ ነው ።

default

ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ የኮሶቮን ጦርነት ለማስቆም ከ12 ዓመት በፊት ጣልቃ ቢገባም በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዩሮ ቢፈስም የጠጠገ የሚመስለው ቁስል በየጊዜው እንደገና የማመርቀዝ አዝማሚያ ማሳየቱ አልቀረም ። ሁለቱ አገራት በመካከላቸው ያለውን አለመግባባት በመፍታት መልካም ግንኙነት እንዲመሰርቱ ከዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ በተለይም ከአውሮፓ ህብረት በኩል በሚደረግ ግፊት ከጥቂት ወራት በፊት መነጋገር ቢጀምሩም ውይይታቸው አንድም ፈር ሳይዝ አዲስ ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተከሌ

Audios and videos on the topic