የሰሜን አፍሪቃ ስደተኞች እና አውሮጳ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 20.04.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የሰሜን አፍሪቃ ስደተኞች እና አውሮጳ

በጣሊያንና በአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት መሀል ስደተኞችን በተመለከተ ውዝግቡ ተካሯል። ጣሊያን ስደተኞቹን ተካፈሉኝ ብትልም ከህብረቱ ሀገራት በኩል የተሰጣት ምላሽ እዚያው እያሉ እናግዝሻለን እንጂ ወደ ሌሎች ሀገራት ስደተኞችን መላክ ተቀባይነት የለውም የሚል ነው።

default

በተለይ ፈረንሳይ እሁድ ዕለት ድንበሯን ሊቋርጡ የነበሩና ከጣሊያን የመጡ ስደተኞችን መመለሷ ውጥረቱን አባብሶታል። የቱኒዚያውን አመጽ ተከትሎ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ቱኒዚያውያን ወደ ጣሊያንዋ የወደብ ከተማ ላምፔዱሳ ገብተዋል። ለእነዚህ ስደተኞች ጊዜያዊ የማቆያ ፈቃድ እሰጣለሁ ብላ ጣሊያን ከገለጸች ወዲህ ፈረንሳይ፤ ጀርመንና ኦስትሪያ በዋናነት ተቃውሞ አንስተዋል።

ባለፈው ዕሁድ በፊንላንድ በተካሄደ ምክር ቤታዊ ምርጫ የቀኜ አክራሪው ፓርቲ እየተጠናከረ መምጣት የሚያስችለውን ድምጽ አግኝቷል። ይኸው « ዘ ትሩ ፊንስ » ወይም እውነተኞቹ ፊንላነዳውያን የተሰኘው ፓርቲ እየተጠናከረ መምጣቱ ለአውሮፓ ህብረት ስጋት ፈጥሯል። ፓርቲው የህብረቱ የድጎማ ፖሊሲን አጥብቆ የሚቃወም መሆኑ በፊንላንድ ምክር ቤት ድምጹ ከፍ ያለ ከሆነ ወደፊት የአውሮፓ ህብረት ኢኮኖሚያቸው ለተናጋባቸው ሀገራት በሚሰጠው ገንዝብ ላይ ጠንካራ አቋም ሊይዝ እንደሚችል ከወዲሁ ተገምቷል።

በዛሬው አውሮፓና ጀርመን በተሰኘው ዝግጅት ጣሊያን በስደተኞች ጉዳይ ከአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ጋር የገጠመችውን ውዝግብና በፊንላንድ የተካሄደውን ምርጫ ይመለከታል።

መሳይ መኮንን

አርያም ተክሌ