የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከአደጋ ነፃ ነው መባሉ | ኢትዮጵያ | DW | 05.07.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከአደጋ ነፃ ነው መባሉ

የኢትዮጵያ የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ መሻሻል በማሳየቱ ለአደጋ የተጋለጡ የዓለም ቅርሶች ከሰፈሩበት መዝገብ ላይ መነሳቱ ተዘገበ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:31

የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከዓለም ለአደጋ ተጋላጭ ቅርሶች መዝገብ መነሳቱ

የኢትዮጵያ የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ መሻሻል በማሳየቱ ለአደጋ የተጋለጡ የዓለም ቅርሶች ከሰፈሩበት መዝገብ ላይ መነሳቱ ተዘገበ። ፓርኩ ከአደጋ ነጻ እንደሆነ የገለጠው የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት በእንግሊዝኛ ምህፃሩ (UNESCO) ነው። ፓርክ ከመጠን በላይ በግጦሽ በመጎዳቱ እንዲሁም  ዋሊያ አይቤክስ፣ የሰሜን ቀይ ቀበሮ እና ሌሎች ግዙፍ አጥቢ እንስሳት ቊጥራቸው በመመናመኑ ነበር ለአደጋ የተጋለጡ የዓለም ቅርሶች መዝገብ ላይ ሰፍሮ የቆየው። የዩኔስኮ ውሳኔ የብዝኃ-ሕይወት ጥበቃው እንዲጠናከር፤ የአገር ጎብኚዎች ፍሰት እንዲቀጥል ትልቅ አስተዋጽዖ ይኖረዋል ሲሉ የፓርኩ ኃላፊ ተናግረዋል። 

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ
 

Audios and videos on the topic