የሰሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ አሁንም እየነደደ ነዉ | ኢትዮጵያ | DW | 15.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የሰሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ አሁንም እየነደደ ነዉ

ለሁለተኛ ጊዜ የተከሰተው እና እስካሁን ሙሉ በሙሉ ሊጠፋ ያልቻለው የሰሜን ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ የእሳት ቃጠሎ ከፍተኛ የሥነ-ምዳር ጉዳት ማስከተሉን የ ፓርኩ የስራ ሃላፊዎች ተናገሩ ፡፡ በስፍራው ቀኝት ያደረገው ዶቼ ቬለ «DW» በተለይ ጭላዳ ዝንጆሮዎች የሚገኙበት የፓርኩ አካባቢ በከፍተኛ መጠን በእሳቱ ውድመት ማስከተሉን ተመልክቷል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:13

ሰንሰለታማዉ ተራራ ላይ የተዛመተዉ እሳት ከፍተኛ ዉድመት እያደረሰ ነዉ

 

ከ 420 በላይ ሄክታር መሬት ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ እስካሁን በብርቅየ እና አጥቢ እንስሳት ላይ ጉዳት ባያስከትልም በብርቅየ እና የፓርኩ መለያ በሆኑ ዛፎች፡ የወፍ ማደርያ ጎጆዎች፡ አይጥ እና ሳር ላይ ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል በማለት የፕርኩ ችፍ ዋርደን አቶ አበባው አዛናው ለ ዶቼ ቬለ «DW» ተናግረዋል፡፡ እሳቱን በማጥፋት ሂደት ከ 7 ሽህ በላይ ህዝብ ተረባርቧል ያሉት የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ለምለሙ ችግሩ አሁን በህብረተሰቡ አቅም መፈታት የማይቻልበት ደረጃ ላይ በመድረሱ የፌዴራል  መንግስት ተለየ ውሳኔ በማሳለፍ ሃብቱን እንዲታደገው ጠይቀዋል፡፡

ግጭ መንደር ላይ የሚገኘው ሙጭላ አፋፍ የተባለው ሰንሰለታማ ተራራ ላይ እየተዛመተ የነበረው እሳት ቁልቁል ከፍተኛ ውድመት እያደረሰ ሲወርድ ከርቀት የ «DW» ዘጋቢ ተመልክቷል፡፡ ይህንን የእሳት አደጋ ለመከላከል የእስራኤል የእሳት አደጋ ተከላካይ ልኡክ ስፍራወ ድረስ ገብቶ ምልከታ እያደረገ ሲሆን የኬንያ ንብረት ነች የተባለች ሰማያዊ በነጭ ቀለም የተቀባች ሄሊኮፍተር ትናንት ስፍራው ድረስ በመሄድ እሳቱን ስታጠፋ እንደዋለች እና ከጎንደር አጼ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ነዳጅ እየቀዳች ወደ ፓርኩ ስትበር ተመልክተናል፡፡

ሰለሞን ሙጬ

 

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ  

Audios and videos on the topic