የሰሜንና የደቡብ ሱዳን ስምምነት እና የኢትዮጵያ ውጉሚ ማብራሪያ | ኢትዮጵያ | DW | 21.06.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሰሜንና የደቡብ ሱዳን ስምምነት እና የኢትዮጵያ ውጉሚ ማብራሪያ

የሰሜን ሱዳን እና የደቡብ ሱዳን መስተዳድር አወዛጋቢውን የአቢየ ድንበር አካባቢ ከጦር ኃይል ተግባር ነጻ የሆነ አካባቢ ለማድረግ ትናንት በአዲስ አበባ በተፈራረሙት ስምምነት መሰረት፡ ኢትዮጵያ አራት ሺህ ሰው ያሰለፈ ጠንካራ ጦር ትልካለች።

default

ይህ ከመሆኑ በፊት ግን የተመድ ጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ተልኮውን ማጽደቅ ይኖርበታል፥ የዩኤስ አሜሪካ ውጉሚ ሂለሪ ክሊንተን ጦሩ ባፋጣኝ እንዲላክ ጠይቀዋል። በተመድ የዩኤስ አሜሪካ አምባሳደር ሱዛን ራይስ ይህን የሚያስችለውን ረቂቅ ውሳኔ ለጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ባስቸኳይ ለማቅረብ እንደሚጥሩ አስታውቀዋል። ወደ አወዛጋቢው የአቢየ ግዛት ይላካል የሚባለው የኢትዮጵያ ጦር ተልዕኮን በተመለከተ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን ስቱድዮ ከመግባታችን በፊት በስልክ አነጋግሬአቸዋለሁ።

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic