የሰማያዊ ፓርቲ ጋዜጣዊ መግለጫ | ኢትዮጵያ | DW | 18.07.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የሰማያዊ ፓርቲ ጋዜጣዊ መግለጫ

ሰማያዊ ፓርቲ ሆን ተብሎ መዋቅራችን እንዲፈርስ እና ፖለቲካዊ ሥራዎችን እንዳንሠራ እየተደረገን ነው ሲል አማረረ። በፓርቲው ላይ የሚፈጸሙ ደባዎች በመላ ሀገሪቱ ቢሆንም በተለይ በአማራ ክልል ግን “ጠንከር፣ ጠጠር ብሏል” ነበር ያሉት የፓርቲው ኃላፊዎች ዛሬ ከሰዓት በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:36

በአማራ ክልል መዋቅራችን እንዲፈርስ እየተደረገ ነው- ሰማያዊ

“እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ዋናው ሥራችን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አላማዎችን ለህዝቡ ማስተዋወቅ መሆን ሲገባው ስራችን እስረኛ መጠየቅ እና ስንቅ ማመላለስ ሆኗል” ብለዋል የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ፡፡ ሁኔታው የከፋው ደግሞ በአማራ ክልል መሆኑን ጠቅሰዋል። “በሀገሪቱ በተለይ በአማራ ክልል የሰማያዊ አባላትን ማሰር እና መዋከብ በከፋ ሁኔታ ቀጥሏል፡፡ ይህንን ከሁለት ወር በፊት ለአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ጥያቄ አቅርበን ነበር፡፡ መልሰን አላገኝም፡፡ ትላንትና ባህርዳር ያሉ አባሎቻችን እና አመራሮች ፍርድ ቤት ቀርበው ነበረ።  ክሱንም አይተነዋል፡፡ የክስ ይዘት የለውም፡፡ ነሐሴ አንድ ቀን 2008 ዓ.ም ባህር ዳር ከተማ በነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት ሰማያዊ ጠርቶ ነበር፣ ህዝብ ራሱ ነው የጠራው በሚል ውዝግብ በዚያ ምክንያት ወደ 20 አባላት ነው የታሰሩት።፡ ባህር ዳር ከተማ ውስጥ ሁሉንም በሚባል መልኩ መዋቅሩን አፍርሰውታል” ብለዋል አቶ የሺዋስ።፡

ዮሃንስ ገብረእግዚያብሔር 

ተስፋለም ወልደየስ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic