የሰማያዊ ፓርቲ የምሥራቅ ጎጃም አስተባባሪ ግድያ | ኢትዮጵያ | DW | 17.06.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሰማያዊ ፓርቲ የምሥራቅ ጎጃም አስተባባሪ ግድያ

ከትናንት በስተያ የተገደለው ወጣት ሳሙኤል ከዚህ በፊት በፀጥታ ኃይሎች መደብደብና መታሰሩን የገለፁት የፓርቲው ሊቀመንበር ጉዳዩ ፖለቲካዊ አንድምታ እንዳለውም ገልጸዋል ።የደብረ ማርቆስ ፖሊስ በበኩሉ የሳሙኤል ገዳይ እጅ ከፍንጅ መያዙን ግድያውንም በገንዘብ መነሻነት መፈጸሙን መናገሩንና ጉዳዩም በመጣራት ላይ መሆኑን ለዶቼቬለ አስታውቀዋል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:22

የሰማያዊ ፓርቲ የምሥራቅ ጎጃም አስተባባሪ ግድያ


ሰማያዊ ፓርቲ ስለ ፓርቲው የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተባባሪ ወጣት ሳሙኤል አወቀ ግድያ ከፖሊስ ግልፅ መረጃ አለማግኘቱን አስታወቀ ። የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ፖሊስ ጉዳዩን እየተከተታተለ መሆኑ ከማሳወቅ ውጭ ለፓርቲው ግልፅ መረጃ እንዳልሰጠ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ። ከትናንት በስተያ የተገደለው ወጣት ሳሙኤል ከዚህ በፊት በፀጥታ ኃይሎች መደብደብና መታሰሩን የገለፁት የፓርቲው ሊቀመንበር ጉዳዩ ፖለቲካዊ አንድምታ እንዳለውም ገልጸዋል ።የደብረ ማርቆስ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ይበልጣል ደምሰው በበኩላቸው የሳሙኤል ገዳይ እጅ ከፍንጅ መያዙን ግድያውንም በገንዘብ መነሻነት መፈጸሙን መናገሩንና ጉዳዩም በመጣራት ላይ መሆኑን ለዶቼቬለ አስታውቀዋል ። ሁለቱን ወገኖች ያነጋገረው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic