የሰማያዊ ፓርቲ የሕግ አገልግሎት ኃላፊ ታሰሩ | ኢትዮጵያ | DW | 20.09.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የሰማያዊ ፓርቲ የሕግ አገልግሎት ኃላፊ ታሰሩ

የሰማያዊ ፓርቲ የሕግ አገልግሎት ኃላፊ አቶ አዲሱ ጌታነህ መታሰራቸዉ ተነገረ። የፓርቲዉ ሊቀመንበር ኢንጂኔር ይልቃል ጌትነት አዳዲስ ከሚባሉት ወጣት አመራሮች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ አዲሱ ትናንት ፍርድ ቤት ቀርበው ሲወጡ ማየታቸውን፤


እና ማዕከላዊ ምርመራ እንደተያዙ ማረጋገጣቸውን ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል። የአቶ አዲሱ ቤተሰቦች በበኩላቸዉ፤ አቶ አዲሱ በባሕርዳር የፓርቲዉ አስተባባሪ ሆነዉ በማገልገል ላይ ሳሉ በተደጋጋሚ ይታሰሩ እንደነበር ገልፀዋል። አቶ አዲሱ ጌታነህ አዲስ አበባ ማዕከላዊ ምርመራ መታሰራቸዉ ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ ቤተሰቦቻቸዉ በጭንቀት ላይ መሆናቸዉን አዲስ አበባ የሚገኘዉ ወኪላችን ዘግቧል።


ዮሐንስ ገብረግዚአብሔር


አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic