የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ፍ/ቤት ቀረቡ | ኢትዮጵያ | DW | 14.03.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ፍ/ቤት ቀረቡ

ባለፈዉ የዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን ዕለት በተደረገዉ ታላቅ ሩጫ ሁከትና ብጥብጥ ፈጥራችኋል በሚል የተከሰሱ ሰባት ሴቶች እና ሶስት ወንዶች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

የአዲስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የካ ምድብ ችሎት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እንደሆኑ በተገለጸዉ ተከሳሾች ላይ ፖሊስ የጠየቀዉን የሰባት ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ዉድቅ በማድረግ አራት ቀናት ብቻ ፈቀደ። የተከሳሾች ጠበቃ የተጠርጣሪዎች የዋስትና መብት እንዲከበር ጠይቀዋል። ፖሊስ በበኩሉ ቢፈቱ ማስረጃዎች ያጠፋሉ ሲል የዋስትና መብት ሊፈቀድ አይገባም በማለት ተከራክሯል።

ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic