የሰማዕታት መታሰቢያ ቀን በአዲስ አበባ | ኢትዮጵያ | DW | 19.02.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሰማዕታት መታሰቢያ ቀን በአዲስ አበባ

ከጥቂት ወራት በፊት ለፋሽስቱ ግራዝያኒ በትውልድ መንደሩ ሃውልትና የመታሰቢያ ሙዝየምም መሰራቱ ኢትዮጵያውያንን አስቆጥቷል። ዛሬ አዲስ አበባ የሰማዕታት መታሰቢያ ዕለትን ምክንያት በማድረግ በተካሄደ ውይይት ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች ለአዶልፍ ግራዝያኒ የተገነቡ መታሰቢያዎች እንዲወገዱ ጠይቀዋል ።

ፋሺሽት ኢጣልያ በ 10 ሺህዎች የሚቀጠሩ ኢትዮጵያውያንን ያለ ርህራሬ የተጨፈጨፈበት 76 ተኛ አመት በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጭ በተለያዩ ዝግጅቶች ታስቧል ። ያኔ በኅይል በተያዘችው በኢትዮጵያ በፋሺሽቱ ጀነራል ግራዝያኒ ላይ በተጣለ ቦምብ መነሻ 3 ቀናት ሙሉ በአዲስ አበባ በተካሄደ የግፍ እርምጃ በበዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአሰቃቂ መንገድ ተገድለዋል በርካታ ቤቶችም በእሳት ጋይተዋል ። ይሁንና ከጥቂት ወራት በፊት ለፋሽስቱ ግራዝያኒ በትውልድ መንደሩ ሃውልትና የመታሰቢያ ሙዝየምም መሰራቱ ኢትዮጵያውያንን አስቆጥቷል። ዛሬ አዲስ አበባ የሰማዕታት መታሰቢያ ዕለትን ምክንያት በማድረግ በተካሄደ ውይይት ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች ለአዶልፍ ግራዝያኒ የተገነቡ መታሰቢያዎች እንዲወገዱ ጠይቀዋል ።  በዚሁ በሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት በተካሄደ ውይይት ላይ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያምን ጨምሮ የፖለቲካ ፓርቲዎች ና የማህበራት ተወካዮች ተገኝተዋል ።

ዮሐንስ ገብረ እግዜዘብሔር

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic