1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰላም ዋጋው ስንት ነው?

እሑድ፣ ሰኔ 30 2016

የክልሉ መንግስት በርካታ ጊዜ የሰላም ጥሪዎችን አስተላልፏል። አሁን በቅርቡ በተካሄደ የሰላም ኮንፈረንስም የሰላም ድምጾች ተሰምቷል። ኮንፈረንሱ ያስተላለፋቸውን ውሳኔዎችን ተከትሎም የሰላም አመቻች ኮሚቴ ተቋቁሞ አሁንም የሰላም ጥሪውን አስተላልፏል።

https://p.dw.com/p/4hvP4
Symbolbild Friedenstaube
ምስል Fotolia/chris-m

የሰላም ዋጋው ስንት ነው?

በአማራ ክልል በመንግስትና በፋኖ ሃይሎች መካከል በተፈረጉና እየተደረጉ ባሉ ውግያዎች በርካቶች ለሞት፣ አካል ጉዳትና መፈናቀል ተዳርገዋል፤ ተማሪዎች ከትምህርት ገባታ ውጭ ሆነዋል፤ በቢልዮን ብሮች የሚገመት ንብረት ወድሟል።
በክልሉ የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሕግ የሚጸናበት ጊዜ አብቅቷል። አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተቀመጠለት ግብ አሳክቷል ወይ የሚለው ጥያቄ የራሱ ጥናት ቢፈልግም ቢያንስ በግልጽ የሚታይ ሐቅ ግን አለ። ጦርነቱን አስቁሞ ሰላም ማስፈን አልተቻለም።
የክልሉ መንግስት በርካታ ጊዜየሰላም ጥሪዎችን አስተላልፏል። አሁን በቅርቡ በተካሄደ የሰላም ኮንፈረንስም የሰላም ድምጾች ተሰምቷል። ኮንፈረንሱ ያስተላለፋቸውን ውሳኔዎችን ተከትሎም የሰላም አመቻች ኮሚቴ ተቋቁሞ አሁንም የሰላም ጥሪውን አስተላልፏል።በዚህ መሃል ግን በየጊዜው እየቀጠለ ባለው ጦርነት የአማራ ሕዝብ ክፉኛ እየተጎዳ እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ። ``የሰላም ዋጋው ስንት ነው`` የዛሬ ውይይታችን ርእስ ነው። የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ሙሉ ውይይቱን ማዳመጥ ትችላላችሁ።


ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር