የሰላም ሚኒስቴር ችግሮችን ለመፍታት እየሰራሁ ነዉ አለ  | ኢትዮጵያ | DW | 07.11.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የሰላም ሚኒስቴር ችግሮችን ለመፍታት እየሰራሁ ነዉ አለ 

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሰላም ሚኒስቴር እና በስሩ የሚገኙት ተጠሪ ተቋማት ደፈር ያለ ሕግን የማስከበር እርምጃ እንዲወስዱ አሳሰበ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:22

«ቋሚ ኮሚቴው የሚኒስቴሩን የሦስት ወራት ሥራ ገምግሟል»

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሰላም ሚኒስቴር እና በስሩ የሚገኙት ተጠሪ ተቋማት ደፈር ያለ ህግን የማስከበር እርምጃ እንዲወስዱ አሳሰበ። ቋሚ ኮሚቶው የሚኒስቴሩን የሦስት ወራት ስራ ሲገመግም እንዳለው ሃገሪቱን ለማተራመስ የሚጥር የተደራጀ ቡድን አለ ብሏል። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንም ሰራዊቱ በተበታተና ሃኔታ እንድልሚገኝና ስራውን ለማከናወን እየገጠመው ያለውን ጣልቃግብነት ቋመልፕ ኮሚቴው እንዲያውቅለት ጠይቊል። የሰላም ሚኒስቴር በበኩሉ በኢትዮጵያ እየተከሰቱ ያሉ የጸጥታ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ወቅታዊ እና አፋጣኝ ምላሽ የሚሹ እና መዋቅራዊ እና በሂደት የሚፈቱ በሚል ለይቶ እየሰራ መሆኑን ገልጿል። ዝርዝሩን  የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ሰለሞን ሙጬ ያቀርበዋል። 

ሰለሞን ሙጬ 
አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ 
 

Audios and videos on the topic