የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት በጀርመን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 29.05.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት በጀርመን

በከፍተኛ ደረጃ የሠለጠነ የሰው ኃይል ከሚያስፈልጋቸው የአውሮፓ አገራት አንዷ ጀርመን ናት ። ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር ፣ ከአንዳንድ የአውሮፓ ሃገራት ወደ ጀርመን የሚፈልሰው ስደተኛ ቁጥር ባለፈው ዓመት ጨምሯል ። የዛሬው አውሮፓና ጀርመን

በከፍተኛ ደረጃ የሠለጠነ የሰው ኃይል ከሚያስፈልጋቸው የአውሮፓ አገራት አንዷ ጀርመን ናት ። ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር ፣ ከአንዳንድ የአውሮፓ ሃገራት ወደ ጀርመን የሚፈልሰው ስደተኛ ቁጥር ባለፈው ዓመት ጨምሯል ። የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን በጀርመን የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጎትና ወደ ጀርመን በሚገባው ስደተኛ ቁጥር መጨመር ላይ ያተኩራል ።

ፒጊ ሙርሞሪ ጡረታ ሊወጡ ተቃርበዋል ። ያለፈው ዓመት ለርሳቸው ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሥራ የበዛበት ዓመት ነበር ። በሚሰሩበት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የምክር አገልግሎት ሰጭ መስሪያ ቤት በየሳምንቱ ምክር ፍለጋ የሚመጡት ስደተኞች ቂጥር ከቀድሞው ጨምሯል ። በርሊን ወደ ሚገኘው መሥሪያ ቤታቸው በየሳምንቱ ብቅ የሚለው ስደተኛ ቁጥር ወደ 20 ይደርሳል ። ከዓመት በፊት ግን በሳምንት የሚያስተናግዱት ስደተኛ  ከ 4 አይበልጥም ነበር ። አብዛኛዎቹ የሚመጡት ከግሪክ ነው ። እርሳቸው እንደሚሉት ወደ በርሊን የሚጎርፈው ስደተኛ ቁጥር  በአሰገራሚ ሁኔታ እያደገ ነው ። የፌደራል ጀርመን ብሄራዊ የስታትስቲክስ ፅህፈት ቤት እንዳስታውቀው በተለይ በእዳ ቀውስ ከተመቱት የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት ወደ ጀርመን የሚመጡት ስደተኞች ቁጥር ክፍ ብሏል ። ምስሪያ ቤቱ እንደሚለው ባለፈው ዓመት ብቻ 24 ሺህ ያህል ግሪካውያን ጀርመን ለመኖርን ለመሥራት መጥተዋል ። ይህ አሃዝም በቀደመው ዓመት ከግሪክ ወደ ጀርመን ከመጡት ጋራ ሲነፃፀር በ 10 ሺህ ከፍ ብሏል ። ይህም በመቶኛ ሲሰላ የ90 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ። ከስፓኝ ወደ ጀርመን የገቡት ስደተኞችም ቁጥር እንዲሁ ከአምናው በ 50 በመቶ አድጓል ።

በአጠቃላይ እጎአ በ 2011 ወደ ጀርመን የፈለሱት አዳዲስ ስደተኞች ቁጥር 958 ሺህ ነው ። ይህም ከቀደመው 2010 ጋር ሲወዳደር የሃያ በመቶ ጨምሯል ። ባለፈው ዓመት በርካታ ቁጥር ያላቸው የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገር ዜጎች ወደ ጀርመን እንዲጎርፉ ምክንያት የሆነው ከአዳዲሶቹ የህብረቱ አባል ሃገራት ማለትም እንደ ፖላንድ ሃንጋሪ እና ሩሜንያ ከመሳሰሉት ከምሥራቅ ና ደቡብ ምሥራቅ አውሮፓ ሃገራት ወደ ጀርመን ለሥራ በሚመጡ አገራት ላይ ጀርመን የጣለችውን እገዳ በ2011 በመነሳቱ ነው ። በዚህ መልኩ በብዛት ወደ ጀርመን ከሚገቡት ስደተኞች አብዛኛዎቹም በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠኑ ባለሞያዎች ናቸው ። የሙርሙሪን ምክር ፍለጋ ብቅ ከሚሉት ውስጥ ከግምሽ በላይ የሚሆኑት በተመሳሳይ ደረጃ ላይ ነው የሚገኙት ።  አብዛናዎቹ በሃገራቸው የሥራ እድል ያላገኙ መሃንዲሶች ሃኪሞች እና በተለያየ ሙያ የሰለጠኑ ምሁራን ናቸው ። ከነዚህም ወጣቶች ያመዝናሉ ። እነዚህን መሰል በከፍተኛ ደረጃ የሠለጠኑ ባለሞያዎች በብዛት ወደ ጀርመን መምጣታቸው የጀረመን አሠሪዎችን አስደስቷል ። ከጀርመን ህዝብ የአብዛኛው እድሜ እየገፋ ሲሄድ የሚተካው ሠራተኛ ኃይል ከአሁኑ በጀርመን አሳሳቢ ሆኗል ። የጀርመን አሠሪዎች ማህበር እንደሚለው  ጀርመን ወደ 2 ሚሊዮን የሚደርስ የሰለጠነ የሰው ኃይል ያስፈልጋታል ። የማህበሩ ፕሬዝዳንት ዲተር ሁንት

Dieter Hundt

ሁንት

« የኤኮኖሚ እድገታችንን የመወዳደር አቅማችንን ብልፅግናችን በአጠቃላይ የሥራ እድል የመፍጠር አቅማችን አሁን ባለበት ደረጃ እንዲቆይ  ከፈለግን ወደፊት ከውጭ የሚመጣ የሰለጠነ የሰው ኃይል ያስፈልገናል ። በሚመጡት ጊዜያት ህንዳውያንን ባለሞያዎች እስካሁን ካደረግነውም በበለጠ ደረጃ ችሎታቸውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ እድል መስጠት አለብን ። በተጨማሪም የሎሎች የውጭ ተወላጅ ሴቶችም ወንዶችም ባለሞያዎች ያስፈልጉናል ።»

የአሰሪዎች አቋም ይህ ቢሆንም ፤ ሃሳቡ በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት የለውም የውጭ ዜጎችን ከመመልመል ይልቅ የራስን ዜጎች አሰልጥኖ መጠቀሙ ሥራ አጥነት ለመቀነስ ይረዳል የሚሉም አሉ ሁንት ግን እነዚህ ተቃዋሚዎች የሚያነሱዋቸውን የመከራከሪያ ሃሳቦችም ውድቅ ነው የሚያደርጉት ።  

እንደ ጀርመን ሠራተኛ ማህበር ፕሬዝዳንት በተለይ ጀርመን በቴክኒኩ መስክ እጅግ የሰለጠነ የሰው ኃይል ትሻለች ። በጀርመንኛው ምህፃር ሚንት ተብለው በሚጠሩት የስራ ዘርፎች ነው ጀርመን የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት ያለባት ። እነርሱም ሂሳብ ኢንፎርሜሽን ሳይንስ የተፈጥሮ ሳይንስና የቴክኒክ ሙያዎች ናቸው ። በነዚህ የሥራ መስኮች የሰለጠኑ ቁጥራቸው ወደ 2 መቶ ሺህ የሚደርስ የሰው ኃይል ነው የሚያስፈልጋት ። ይህ ጉድለትም በተቻለ መጠን መሞላት ይኖርበታል እንደ ሁንት የስስለዚህ ሁንት እጅግ አስፈላጊ ሆኖ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው እነዚህን ባለሞያዎች ጀርመን በመምጣታቸው ደሰተኛ መሆናናችንን ማሳየትና በጥሩ ሁኔታም መቀበልና መያዝ ይገባናል ይላሉ ። ይሁንና ጀርመን ለሚመጡ አዳዲስ ስደተኞች ሁሉ ሁኔታዎች እንዲህ ቀላል አይደሉም ።

Qualifizierung Zuwanderung Deutschland Arbeitsmarkt

ሙርሙኒ እንደሚሉት ስደተኞቹ የጀርመንኛ ቋንቋና ባህልንም ማጥናት ይኖርባቸዋል ። ይህም በርሳቸው አስተያየት ሥራ ፈላጊዎቹ ከሃገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር እንዲላመዱ የሚረዳ በጣም ጥሩ እገዛ የሚያደርግም መንገድ ነበር ሆኖም   ከዚህ ቀደም ከአውሮፓ ሃገራት ለሥራ ወደ ጀርመን የሚመጡ ስደተኞች የተለያዩ ማህበራዊ ጥቅማ ጥቅሞችን ያገኙ ነበር ፤ የጀርመንኛ ቋንቋ ና  ከህብረተሰቡ ጋራ ተዋህዶ መኖር ላይ ያተኮረ ትምህርትም ያገኙ ነበር ። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ግን ይህ በመቅረቱ ሥራ ፍለጋ ከሌሎች የአውሮፖ ህብረት ሃገራት ጀርመን ለሚመጡ ስዎች ሁኔታዎች አሰቸጋሪ መሆናቸው አልቀረም ።

ሙዚቃ ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።    

በጀርመን በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጎትን ከአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት ብቻ ማሟላት የማያቻል በመሆኑ የጀርመን መንግሥት በምሁራን ምልመላ ረገድ ከህብረቱ አባል  ሃገራት ውጭም እያተኮረ ነው ። በዚህ በኩል የውጭ ዜጎች በአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራትም ሆነ በጀርመን  ለተወሰነ ጊዜ መሥራት የሚያስችላቸው ፈቃድ ወይም ሰማያዊ ካርድ ሥራ ላይ መዋሉ የውጭ ዜጎች ወደ አውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት የሚገቡበትን ሁኔታ አቅሎታል ። የዚህ ፍላጎት ያላቸው የውጭ ዜጎች የትምህርት መረጃቸውን ካሰመረመሩና  በዓመት  44,800 ዩሮ ወይም 57,050 ዶላር ደሞዝ የሚያገኙበት የሥራ ውል እንዳገኙ ካረጋገጡ በአበህብረቱ አባል ሃገር መኖርም ሆነ መሥራት  ይችላሉ ። በዚሁ ፈቃድ መሠረት ብዙ ሠራተኞች በሚያስፈልጉባቸው የሥራ መስኮች የውጭ ዜጎች ከ3 ዓመት ቆይታ በኋላ ለራሳቸውና ለቤተሰባቸው ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት ማመልከትም ይችላሉ ። የጀርመን አሠሪዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ሁንድት ይህ በከፈተኛ ደረጃ ለሰለጠኑ የውጭ ዜጎች የወጣው ደንብ ከነዚህኞቹ ያነሰ ደረጃ ያላቸው  ሰዎችም ማካተት አለበት ይላሉ ። ከዚህ ሌላ ጀርመን ለኤኮኖሚ እድገትዋ እጅግ አስፈላጊ የሆነውን የሰው ኃይል ለማሟላት ወደ ሃገርዋ የሚመጡትን የውጭ ሠራተኛ ኃይል በአግባቡ ማስተናገድ ይገባታልም ነው የሚሉት ።

Flash-Galerie Fachkräftemangel

« በመጀመሪያ ማለፊያ የሆነ የእንግዳ አቀባበል ባህል መፍጠር አለብን ። ከሌሎች ሃገሮች በተለይም ደግሞ ከአውሮፓ ህብረት ውጭ የሚመጡ የውጭ ዜጎች በአጣዳፊ ሁኔታ እንደምንፈልጋቸው ለማሳወቅና እንኳን ደህና መጣችሁ የሚል ምልክት ማሳየት አለብን ።ባለፉት ጊዜያት በርግጥ ማንኛውንም አጋጣሚ መርምረን አልተጠቀምንበትም ። ለኔ ይህ  ጊዜያዊ በጎ እርምጃ ነው ። አሁን ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ እያመራን በመሆናችን እፎይታን የሚያስገኝ ጎዳና ላይ ነው ።»

በሁንት አባባል ሌላው የተለወጠ አሠራርም ለውጭ ዜጎች ሁኔታዎችን አቅሏል  

« በባለሞያዎች እንዲያዙ በሚፈለጉ የሥራ ቦታዎች ተስማሚ የሆነ የሃገሬው ተወላጅ ለማስቀደምም ልዩነት የሚያደርግ ፈተና መቅርቱ ማለፊያ ነው ። የአውሮፓ ህብረት ተወላጆች ያልሆኑ ወደ ጀርመን ሲመጡ በቀጥታ ሥራ መጀመር ሳይሆን ለ 6 ወር በሥራ ፍለጋ እንዲቆዩ የሚያስገድደው አሠራር መቅረቱም ሌላው አዎንታዊ ሂደት ነው ። ዋናው ጠቃሚው ጉዳይ እውነተኛ የሆነ የእንግዳ ተቀባይነትን ባህል መፍጠሩና እነዚህን ሰዎች በዚህ በሃገራችን በጀርመን ቢቆዩ ደስተኞች መሆናችንን ማሳየቱ ላይ ነው ።»

ሙርሙሪ እንደሚሉት ከአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራትም ሆነ ከሌላው የዓለም ክፍል ወደ ጀርመን የሚመጡ ስደተኞች በመጀመሪያ መረጃ ያስፈልጋቸዋል ። መብቶችና ግዴታዎቻቸውን ማወቅ የት ማመልከት እንደሚችሉም እንዲሁ አዳዲስ ስደተኞች የሚያነሱዋቸው ጥያቄዎች ናቸው ። አንዳንዶቹ እንዲያውም ካሉበት አገር ሳይነሱ ነው አስቀድመው ጥያቄውን የሚያቀርቡት ሆኖም በርሳቸው አገላለፅ በጀርመን ፌደራል ሪፕብሊክ ይህን መሰሉ መረጃ የሚገኝባቸው መስሪያ ቤቶች ጥቂት ናቸው ። ሆኖም አሁን የፌደራል ጀርመን መንግሥት የሠራተኞች ጉዳይ መሥሪያ ቤት በርካታ ሠራተኞች ከሚጎርፉበት ከግሪክ ባለሥልጣናት ጋር በቅርበት እየሠሩ ነው ። ያም ሆኖ በአጠቃላይ ሲታይ ጀርመን በዚህ ረገድ የምታደርገው እንቅስቃሴ እንደ ሙርሙሪ አዝጋሚ ነው ። በርሳቸው አስተያየት ፈጥኖ መንቀሳቀስ ካልተቻለ ጀርመን ልታገኝ የምትችለውን አስፈላጊ የሰው ኃይል ማጣቷ አይቀርም ። በከፍተና ደረጃ የሰለጠኑት ምሁራን ጀርመን አስፈላጊውን መረጃም ሆነ መስተንግዶ ካላገኙ ወደሌላ ቦታ መሄዳቸው ሳይታለም የተፈታ ነው ።  

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 29.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/1549F
 • ቀን 29.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/1549F