የርዳታ ጥሪ ለቻድ ሃይቅ አዋሳኝ ሃገሮች | አፍሪቃ | DW | 26.05.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የርዳታ ጥሪ ለቻድ ሃይቅ አዋሳኝ ሃገሮች

የቻይድ ሃይቅን በሚያዋስኑ አካባቢዎች የሚኖረዉ ወደ 30 ሚሊዮን ሕዝብ ለከፍተኛ ችግርና ረሃብ መጋለጡ ተገለፀ። የቻድ ሐይቅ የዉኃ መጠን በመቀነሱ በሕይቁ ዙሪያ፤ በሰሜን ምሥራቅ ናይጀርያ፤ ሰሜን ካሜሩን፤ ምዕራብ ቻድና፤ ደቡብ ምሥራቅ ኒጀር የሚኖሩ ሰዎች ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:12
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:12 ደቂቃ

የቻድ ሃይቅ አዋሳኝ ሃገሮች

ከዉኃዉ ማነስ በተጨማሪ ባካባቢዉ የሚካሔደዉ ግጭት የነዋሪዎቹን ጭግር ማባባሱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታዉቋል። ጽንፈኛዉ ቡድን ቦኮሃራም ባለፉት ሰባት ዓመታት በቻድ ሃይቅ አዋሳኝ ሃገራት 15 ሺህ ሰዎችን መግደሉ ተዘግቦአል። የቻድ ሃይቅ አዋሳኝ ሃገራት መካከል የሚታየዉ ችግር በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ችላ ተብሎአል በሚል ከፍተኛ ቅሪታ ቀርቦአል። በያዝነዉ ሳምንት ኢስታንቡል-ቱርክ በተሠየመዉ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ የቻይድ ሃይቅ አዋሳኝ ሃገራት ችግርና ረሃብ ተነስቶ ነበር። የቻይድ ሃይቅ አዋሳኝ ሃገራት ችግርና ረሃብ ጉዳይ ናይሮቢ ኬንያ የሚገኘዉን ወኪላችንን በስልክ አነጋግረነዉ ነበር።

ፋሲል ግርማ

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic