የርዕዮተ ዓለሙ መሸለም | ኢትዮጵያ | DW | 17.04.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የርዕዮተ ዓለሙ መሸለም

የተባበሩት መንግሥታት የትምሕርት፥ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (UNESCO በምሕፃሩ) እንዳስታወቀዉ ርዕዮት የተሸለመችዉ፥ ለፕረስ ነፃነት ባሳየችዉ ቁርጠኝነት፥ ትግልና ፅናት ነዉ

በእሥር ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያዊቷ አምደኛና ፀሃፊ ርዕዮት አለሙ ፣ የተባበሩት መንግሥታት የትምሕርት የሳይንስና የባህል ድርጅት በእንግሊዘኛው ምህፃር ዩኔስኮ በየአመቱ የሚሰጠውን የአለም የፕሬስ ነፃነት ሽልማት አገኘች ። ርዕዮት አለሙ ሃሳብን በነፃነት ለመግለፅ ባሳየችው ልዩ ቁርጠኝነት ትግል ና ፅናት በድርጅቱ የመገናኛ ብዙሃን ዳኞች ለሽልማቱ እንደተመረጠች ዩኔስኮ አስታውቋል ።ዳኞቹ ርዕዮት ለተለያዩ የግል የህትመት ውጤቶች ያበረከተችውን አስትዋፅኦም ከግምት ውስጥ ማስገባታቸውን ድርጅቱ አስታውቋል ። ርዕዮት አለሙ በአሸባሪነት ተወንጅላ በይግባኝ 5 አመት እሥራት ተፈርዶባት በእስር ላይ ትገኛለች ።

ሽልማቱ የፊታችን ሚያዚያ 25 2005 አም ኮስታሪካ ውስጥ እንደሚሰጥ ዩኔስኮ አስታውቋል ።ርዕዮት የተለያዩ መጣጥፎችን በተከታታይ ታሳትምበት የነበረዉ እና አሁን መታተሙ ያቆመዉ የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ ሽልማቱ ለርዕዮት ብቻ ሳይሆን ለመላዉ ነፃ ኢትዮጵያዉያን ጋዜጠኞች እንደተሰጠ የሚቆጠር ነዉ።ሽልማቱ ለርዕዮት እንዲሰጥ የወሰኑት ዳኞች ሊቀመንበር ማንዱራል አርሹዋን የኢትዮጵያ መንግሥት ርዕዮት ዓለሙን ከእስር ቤት ለቅቆ ተሸላሚዋ ሽልማቱን በአካል ተገኝታ እንድትቀበል ጠይቀዋል።የዩኔስኮ የፕሬስ ነፃነት ሽልማት በተለይ ራሳቸውን ለአደጋ አጋልጠው በማንኛውም የአለም ክፍል ሃሳብን በነፃነት ለመግለፅ ለሚታገሉ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች የሚሰጥ ሽልማት ነው ።የፓሪሷ ወኪላችን ሐይማኖት ጥሩነሕ ዝር ዝር ዘገባ ልካልናለች።

ሐይማኖት ጥሩነሕ

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ

Audios and videos on the topic