የርዋንዳ የጎሣ ጭፍጨፋ አሥረኛ ዓመት መቃረብ | የጋዜጦች አምድ | DW | 28.02.2004
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የጋዜጦች አምድ

የርዋንዳ የጎሣ ጭፍጨፋ አሥረኛ ዓመት መቃረብ

የርዋንዳ ጭፍጨፋ የተጀመረበት ዕለት አሥረኛ ዓመት ሊሞላው አምስት ሣምንታት በቀረው ባሁኑ ጊዜም ጭፍጨፋው በሀገሪቱ ትቶት ያለፈው መዘዝ ገና ጨርሶ አልተወገደም። ፕሬዚደንት ፖል ካጋሜ የሚመሩት መንግሥት በሁለቱ የሀገሪቱ ጎሣዎች፡ ብዙኃኑ ሁቱዎችና ውሁዳኑ ቱትሲዎች መካከል ዕርቀ ሰላም ለማውረድ ያነቃቃው ጥረቱም አዳጋች እንደሆነ ይገኛል። የርዋንዳን የጎሣ ጭፍጨፋ እንዲመረምር እአአ በ 1994 ዓም የተቋቋመው ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት፡ ሳያመልጡ የተያዙትን ቀ

��ደኞቹን የጭፍጨፋው ጠንሳሾችን ጉዳይ ማጣራት የቀጠለ ሲሆን፡ እአአ እስከ 1994ዓም ድረስ ሥራውን ለማጠናነቅ ያቀደው ይኸው ፍርድ ቤት እስካሁን ከቀረቡለት ሀያ አንድ ክሶች መካከል ለአንድ ሦስተኛው ብያኔ ሰጥቶዋል። ከጭፍጨፋው በኋላ በሀገር ውስጥ የተቋቋሙት ባህላዊ ፍርድ ቤቶች ደግሞ ወህኒ ቤቶችን ያጨናነቁትን በጭፍጨፋው ተሳተዋል ተብለው የተጠረጠሩትን ዘጠና ሺህ እሥረኞችን ጉዳይ እያዩ፡ ጥፋተኛ ሆነው ያገኙዋቸውን ከኅብረተ ሰቡ ጋር የሊዋኃዱ የሚችሉበትን ቅጣት እየሰጡ ለችግሮች መልስ ለማስገኘት ይጥራሉ። ጥረቱ በሁቱና በቱትሲ ጎሣዎች መካከል ያለውን ልዩነት ያስወግዳል ተብሎ ተስፋ ተደርጓል።