የርዋንዳ እና የጀርመን ግንኙነት | አፍሪቃ | DW | 09.02.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የርዋንዳ እና የጀርመን ግንኙነት

ርዋንዳ እንደገና ከጀርመን የገንዘብ ርዳታ እንደምታገኝ ተገለጸ። የጀርመን የልማት ተራድዖ ሚንስቴር ባለፈው ሣምንት በበርሊን ከርዋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሉዊዝ ሙሽኪዋቦ ጋ ሀሳብ ከተለዋወጠ በኋላ እዚህ ውሳኔ ላይ መድረሱን አመልክቶዋል።

አንድ የተመድ የጠበብት ቡድን ርዋንዳ በምሥራቃዊ ዴሞክራሲያዊ ኮንጎ ሬፓብሊክ በመንግሥቱ አንፃር የሚዋጉትን ራሱን « ኤም 23 ብሎ የሚጠራው ቡድን ዓማፅያንን እንደምትረዳ ያስታወቀበትን ትናት ይፋ ካደረገ በኋላ የጀርመን መንግሥት ለርዋንዳ ይሰጠው የነበረውን ሰባት ሚልዮን ዩሮ የበጀት ርዳታ ማቋረጡ ይታወሳል።

ፊሊፕ ዛንደር/አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic