የሪዮው ኦሎምፒክ እና ዚካ | ጤና እና አካባቢ | DW | 06.06.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ጤና እና አካባቢ

የሪዮው ኦሎምፒክ እና ዚካ

ብራዚል ሪዮ ደጀኔሮ የሚካሄደው የኦሎምፒክ ጨዋታ ወደ ሌላ አገር እንዲዛወር አለያም ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ከአንድ ሳምንት በፊት የቀረበው ጥያቄ በዓለም የጤና ድርጅትና በአንዳንድ የጤና ባለሞያዎች ተቀባይነት ባያገኝም የዓለም የጤና ድርጅት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ጉዳዩ እንደገና እንዲጤን ጠይቋል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:56

የሪዮው ኦሎምፒክ እና ዚካ

ከ100 በላይ የጤና ባለሞያዎች ለዓለም የጤና ድርጅት በፃፉት ግልፅ ደብዳቤ፣የኦሎምፒክ ጨዋታው በሃገሪቱ የተከሰተው የዚካ ቫይረስ ወረረሽኝ በሌላው የአለም ክፍል እንዲስራጭ ምቹ አጋጣሚ ይፈጥራል የሚል ስጋታቸውን አስፍረዋል ። ቀደም ሲል ጉዳዩ አስጊ እንዳልሆነ የገለፀው የዓለም ጤና ድርጅት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ግን የጤና ባለሞያዎች ቡድን ጨዋታው በተያዘለት የጊዜ ሠሌዳ ይካሄድ አይካሄድ የሚለውን እንደገና እንዲያጤኑ ጠይቋል ። ሆኖም ስለ ጉዳዩ ዶቼቬለ የጠየቃቸው አንድ የጀርመን ሳይንቲስት ግን ጨዋውን መግፋት ወይም ወደ ሌላ አገር መግፋት አይገባም ።
ከአንድ ሳምንት በፊት ነበር ከ 150 በላይ የሚሆኑ ሳይንቲስቶችና የህክምና ባለሞያዎች የፊታችን ሐምሌ መጨረሻ ላይ ሪዮ ደጀኔሮ የሚካሄደው የኦሎምፒክ ጨዋታ ወደ ሌላ አገር እንዲዛወር አለያም ለሌላ ጊዜ እንዲገፋ የጠየቁት ። የህክምና ባለሞያዎቹ ለዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት ሃላፊ ማርጋሬት ቻን በላኩት ደብዳቤ ከመላው ዓለም በውድድሩ ለመሳተፍ እና ጨዋታውን ለመከታተል ወደ ብራዚል የሚሄዱ ግማሽ ሚሊዮን እንደሚሆኑ የሚገመቱ ሰዎች ብራዚል ውስጥ በወረርሽኝ መልክ በተቀሰቀሰው የዚካ ቫይረስ ሊያዙ እና ወደ ሃገራቸው ሲመለሱም ቫይረሱን ሊያሰራጩ እንደሚችሉ ያላቸውን ስጋት ገልፀዋል ። በዚህ ምክንያትም ጨዋታው ከርዮ ደጀኔሪ ወደ ሌላ አገር እንዲዛወር አለያም ቀኑ እንዲገፋ ፊርማቸውን ባሰፈሩበት ደብዳቤ

Brasilien Zika Virus - Mikrozephalie - Mutter mit Baby

ማርግሬት ቻን የዓለም ጤና ድርጅት ሃላፊ

ጠይቀዋል ። ይሁንና የዓለም የጤና ድርጅት የጤና ባለሞያዎቹን ጥያቄና ስጋት በወቅቱ ውድቅ አድርጎታል ።ድርጅቱ እንዳለው የርዮው ጨዋታ መሰረዝ የዚካን ስርጭት ሊገታ አይችልም ። ምክንያቱም እንደ ድርጅቱ በትንኝ አማካኝነት የሚተላለፈው ቫይረሱ በአሁኑ ጊዜ በ60 ሃገሮች ውስጥ ይገኛልና ። እንደ ዓለም የጤና ድርጅት ሁሉ በወቅቱ አንዳንድ ሳይንቲስቶችም የጤና ባለሞያዎቹን ስጋት አጣጥለዋል ። ከመካከላቸው አንዱ ጀርመናዊው ሳይንቲስት ዮናስ ሽሚት ቻናዚት ናቸው እርሳቸው እንደሚሉት ጨዋታውን በመግፋት የዚካን ቫይረስ ሥርጭት መግታት አይቻልም
«እጅግ በጣም የተወሳሰበ ሁኔታ ነው ። ጨዋታውን ወደ ሌላ ጊዜ በማዛወር ችግሩ ይፈታል ማለት አይደለም ።የዚካ ቫይረስ በሌሎች በርካታ ሃገራትም ይገኛል ። በርግጥ የኦሎምፒክ ጨዋታው በተለይ የቫይረሱ ሥርጭት ወደ አውሮጳ እንዲጨምር ያደርጋል ።ይህን ማንም አይክድም ። ሆኖም ብራዚል ውስጥ በተሰራጨበት ደረጃ አውሮጳ ውስጥ ጉዳት ያደርሳል ማለት አይደለም ። »
ዚካ በተባለው ቫይረስ የሚያዙ እናቶች ከተለመደው ያነሰ የራስ ቅል ያላቸው እድገታቸውም ችግር ያለበት ህጻናት ነው የሚወልዱት ። ብራዚል ውስጥ ቫይረሱ በወረርሽኝ ከተከሰተበት ካለፈው ዓመት አጋማሽ ወዲህ 1300 ህፃናት ከዚህ የጤና ችግር ጋር ተወልደዋል ። ለዓለም የጤና ድርጅት ደብዳቤ የፃፉት የጤና ባለሞያዎች ዚካን ከብራዚል ለማጥፋት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም በቫይረሱ የሚያዙት ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው ይላሉ ።በነርሱ አስተያየት ከሁለት ወራት በኋላ በሪዮ ደጀኔሮ የኦሎምፒክ ጨዋታ መካሄዱ በሚነድ እሳት ላይ ቤንዚን እንደመጨመር የሚቆጠር ነው ። ዶክተር ዮናስ ሽሚት ቻናዚት ግን የተለየ አስተያየት ነው ያላቸው ።
« የኦሎምፒክ ጨዋታዎች የሚካሄደው በጣም ጥቂት ትንኞች በሚገኙበት በበብራዚል የክረምት ወቅት መሆኑንም መገንዘብ

Zika Virus WHO Margaret Chan

በዚካ ቫይረስ ከተያዘች እናት የተወለደ ህፃን

አለብን ። ከዚህ በተጨማሪ ጨዋታው ወደ ሌላ አገር ከተዛወረ ብራዚል ለምሳሌ በሽታውን ለመከላከል ልትጠቀምበት የምትችለውን ከፍተኛ ገቢ ነው የምታጣው ። »
የዚካ ቫይረስን የመሳሰሉ ተላላፊ የጤና ችግሮች ሲከሰቱ ታድያ ምንድነው መደረግ ያለበት ዶቼቬለ ለዮናስ ሽሚት ቻናዚት ያቀረበው ጥያቄ ነበር
«ሊያስከትል የሚችለው መዘዝ ምንድን ነው የሚለውን ጥያቄ ማንሳት ያስፈልጋል ።ዋና ዋና የስፖርት ውድድሮችን ሁሉ መሰረዝ አይቻልም ። ይህ ውጤታማ አይደለም ።ከዚያ ይልቅ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ አስቀድሞ መመዘን ያስፈልጋል ።ይህንንም የዓለም የጤና ድርጅት አከናውኗል ፣የአውሮፓ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ማዕከልም ይህን አካሂዷል፣የጀርመኑ የሮበርት ኮህ ተቋምም እንዲሁ ይህንኑ ሰርቷል ። አንዳቸውም የኦሎምፒክ ጨዋታው ይሰረዝ የሚል ውሳኔ ላይ ግን አልደረሱም ።»
ዚካ አስጊ መሆን አለመሆኑን ለመፈተሽ 4 ጊዜ ያህል ከፍተኛ ሳይንቲስቶችን ወደ ብራዚል የላከውና አስጊም አይደለም ብሎ የነበረው የዓለም የጤና ድርጅት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የጤና ባለሞያዎች ቡድን ጉዳዩ እንደገና እንዲያጤን ጠይቋል ። WHO ውሳኔው እንደገና እንዲን የወሰነው ከአሜሪካን ሴናተር ጄአን ሻሂን ፣የሮዮው ኦሎምፒክ ሐምሌ መጨረሻ መካሄዱ ሊያስከትል የሚችለው የበሽታው ስርጭት ስጋት እንዲጠና ከጠየቁ በኋላ ነው ።

ኂሩት መለሰ

አርያም አብርሃ

Audios and videos on the topic