የሩዋንዳ ተቃዋሚዎች ችግር | አፍሪቃ | DW | 18.10.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የሩዋንዳ ተቃዋሚዎች ችግር

በሩዋንዳ መንግስትን ተቃውሞ መናገር አስፈሪ ጉዳይ ነው። በተለይም እነ ቪክቶሪ እንጋቢሬ፣ ዲዮ ሙሻዪዲና በርናንድ ንታንጋዳ ለመሳሰሉ የመንግስት ተቃዋሚ ፖሊተከኞችደግሞ ጉዳዩ ከበድ ይላል። ሙሻይዲ ላይ የእድሜ ልክ እስራት፣ ንታጋንዳ ደግሞ የአራት ዓመት እስራት ተበይኖባቸዋል።

ለአስራ ስድስት ዓመታት ኒዘርላንድ ውስጥ በስደት ከኖሩ በኋላ ነበር ሩዋንዳዊቷ ተቃዋሚ ፖሊቲከኛ ቪክቶሬ እንጋቢሬ ወደ ሀገራቸው እአአ በ2012 መጀመሪያ ላይ የተመለሱት። ይህም የተባበሩት ዲሞክሲያዊ ኃይሎች በምህጻር FDUን እንኪንጊን ወክለው በሩዋንዳው ፕረዚዳንታዊ ምርጫ ለመወዳደር ነበር። ሆኖም ፓርቲያቸውና ሌሎች ሁለት ትላልቅ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በምርጫው እንዲሳተፉ አልተፈቀደላቸውም። እንጋቢሬም ታስረዋል። የFDU እንኪንጊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመምበር ኡጎኔ እንዳዮ፣ ይህ ተቃዋሚዎችን ከምርጫው ለማግለል የተወሰደ እርምጃ ነው ይላሉ፤

«ይህ ከገዢው ፓርቲ የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር ፓርቲ ወይም FPR ጨቋኝ ሥርዓት ጋር የተያያዘ ነው። ይህ ፓርቲ የሚያስተዳድረው በሽብር ነው። ተቃዋሚዎችን ወደ ውጭ ሀገር ያሳድዳል። የተቃዋሚ ፓርቲዎችን የሚበታትንበት ትልቅ የገንዘብ አቅምም አለው። ለዛ ነው ብዙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ፖሊቲከኞች ከሀገር ውጭ ተሰደው ሌላ ሀገር ያሉት። ለዛ ነው አብዛኞቻቸው ተደራጅተው መንቀሳቀስ የሚሳናቸውና ሲያስፈልግም ከFPR ወንጀለኛ ኃይል ራሳቸውን መከላከል የሚያቅታቸው።»

ኡጎኔ እንዳዮም ቢሆኑ የFDU እንክሊንጊ ፓርቲ ሥራዎችን ፈረንሳይ ተቀምጠው ይሰራሉ። ዲዮ ሙሻይዲ የተባሉ ተቃዋሚ ፖሊቲከኛ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ አሰራጭተሃል በሚል ክስ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው ወይኒ ቤት ተወርውረዋል። ቤርናንድ እንታንጋንዳ የተባሉ ሌላ ፖሊቲከኛም እንደ እንጋቢሬ ሁላ ፕሬዚዳንት ፖውል ካጋሜን በ2010 ተፎካክረው ነበር። ተቀባይነት ያላገኝ ስላማዊ ሰልፍ አቀናጅተሃል በሚል ክስ አራት ዓመት ወይኒ ቤት እንዲያሳልፉ ተፈርዶባቸዋል።

ቪክቶር እንጋቢሬ ከስደት ከተመለሱ ወዲህ፣ በሩዋንዳ ጭፍጨፋ በሁቱ ህዝቦች ላይ የደረሰ ግድያም ትኩረት እንዲያገኝና በህግ እንዲዳኝ ጠይቀዋል። ለዚህ ነበር ሁቱዎች በቁጥር አናሳዎቹ የቱሲ ጎሳዎች ላይ ያደረሱትን ጭፍጨፋ ክደዋል በመባል የተከሰሱት።

Bujumbura Hauptstadt von Burundi

የሩዋንዳ ነጻነት ዲሞክራሲያዊ ኃይል ወይም በምህጻር FDLR የሚባል የሁቱ አማጺያን ቡድንን በገንዘብ መደገፍ፣ ያገሪቷን ደህንነት አደጋ ላይ መጣልና፣ ህዝብ መንግስት ላይ ለአመጽ እንዲነሳሳ መቀስቀስ የሚሉ ነበር በሴት ፖሊቲከኛዋ እንጋቢሬ ላይ የቀረቡ ሌሎች የክስ ምክንያቶች። ለዛ ነበር የሩዋንዳ አቃቤ ህግ ቢሮ በቪክቶሪ እንጋቢሬ ላይ የእድሜ ልክ እስራት እንዲፈረድ የጠየቀው። በጀርመን የሃምቡርግ ማህበራዊ ጥናት ተቋምና ተመራማሪና የሩዋንዳ ጉዳይ ባለሙያው ጌርድ ሃንከል የሩዋንዳ መንግስት ከረዥም ጊዜያት ጀምሮ በተቃዋሚዎች ላይ ይወስድ የነበረውን ጠንከር ያለ እርምጃ አስተውለዋል፣

«በጠቅላላ አሁን እየተሰራበት ያለውና እነ ቪክቶሪ እንጋቢሬ የተከሰሱበት ከፍተኛው የእስራት ቅጣት፣ በሩዋንዳ ውስጥ የተቃዋሚ ፓርቲ ሆኖ መንቀሳቀስ እንደማይቻል አመልካች ነው።»

ሃንከል በሩዋንዳ መንግስት በተቃዋሚዎቹ የሚያደርሰው በደል እስካልተለወጠ ድረስ ተቃዋሚዎቹ በራሳቸው አንድ ነገር ማድረግ መቻላቸውን ይጠራጠራሉ።

Ruanda Präsidentschaftswahl 2010 Afrika Kigali«መንግስት ከሚቀበላቸው ሐሳቦች የተለዩ አስተሳሰቦች ሲነሱ፣ ገዢው ፓርቲ በስሜታዊነትና በጠላትነት ስሜት የሚያያቸው ከሆነ የሩዋንዳ ተቃዋሚ ፓርቲ የወደ ፊት ጉዚ ጨለማ ይመስለኛል። ይህ እየሆነ ነው። መንግስትን የሚቃወሙ አስተሳሰቦች አያስፈልጉም። መንግስትም ሐሳቦቹን ከመፋለም ወደኋላ አይልም።

የፓውል ካጋሜ መንግስት ግን በተቃዋሚዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ ህጋዊ ነው እንጂ ፖሊቲካዊ እርምጃ አይደለም ይላል።

ገመቹ በቀለ

አርያም ተክሉ

Audios and videos on the topic