የሩዋንዳ ምርጫ ዉጤት | አፍሪቃ | DW | 08.08.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የሩዋንዳ ምርጫ ዉጤት

አርብ በተደረገዉ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ሩዋንዳን በተዘዋዋሪም-በቀጥታም ለ23 ዓመታት የመሩት ፕሬዝደንት ፖዉል ካጋሜ እንደተጠበቀዉ በ99 ከመቶ ድምፅ ዘመነ ሥልጣናቸዉን አራዝመዋል

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:46

ካጋሚ በ99 ከመቶ ድምፅ «ተመረጡ»

ኬንያዎች የወደፊት መሪዎቻቸዉን ለመምረጥ ዛሬ ድምፅ ሲሰጡ፤ ሩዋንዳዎች አርብ በሰጡት ድምፅ ዉጤት ደስታ ወይም ሐዘናቸዉን እየገለጡ ነዉ።አርብ በተደረገዉ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ሩዋንዳን በተዘዋዋሪም-በቀጥታም ለ23 ዓመታት የመሩት ፕሬዝደንት ፖዉል ካጋሜ እንደተጠበቀዉ በ99 ከመቶ ድምፅ ዘመነ ሥልጣናቸዉን አራዝመዋል።ካጋሜ የትንሺቱን ምሥራቅ አፍሪቃዊት ሐገር የዘር መጠፋፋት ያስቆሙ፤ ሠላም ያሰፈኑ፤ ምጣኔ ሐብቷን ያሳደጉም ተብለዉ ይወደሳሉ።የዚያኑ የክል ለተቃዋሚዎቻቸዉና ለመብት ተሟጋቾች ምሕረት የሌላቸዉ ጨካኝ አምባገነን ተብለዉ ይወቀሳሉ።ዩናይትድ ስቴትስና የአዉሮጳ ሕብረት ከጋሜ መንግሥት ጋር ተባብረዉ እንደሚሰሩ በየፊናቸዉ አስታዉቀዋል።

 

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic