የሩዋንዳ ልማት የገንዘብ ተቋም | አፍሪቃ | DW | 29.11.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የሩዋንዳ ልማት የገንዘብ ተቋም

ገና ከጅምሩ በመዋጮ ማሰባሰቡ ዘመቻ ላይ ትችቶች እየተሰነዘሩ ነው ። መገናኛ ብዙሃን እንደሚሉት መዋጮው ሁልጊዜም በፈቃደኝነት አይደለም የሚሰጠው ። ሃብታም ሩዋንዳውያን ከገቢያቸው 10 በመቶ እንዲያዋጡ ይጠበቃል ። ከዚህ ሌላ በዚህ መዋጮ የማይሳተፉት የሚገጥማቸው ማህበራዊ ጫናም ከፍተኛ መሆኑን ነው ታዛቢዎች የሚናገሩት ።

የፋይናንስ ሃላፊነቶችን መሸከም ፣ ልማትን በማፋጠን ከልማት እርዳታ ጥገኝነት መላቀቅ ናቸው በእንግሊዘኛው ምህፃር «አጋሲሮ » በመባል የሚታወቀው የመጀመሪያው የሩዋንዳ የልማት ትብብር የገንዘብ ተቋም ግቦች ። ሩዋንዳ ለዚህ ግብ ማስፈፀሚያ የሚውለውን ገንዘብ ለማግኘት የምታስበው ከህዝቡ መዋጮ ነው ። ግን በርግጥ ገንዘቡ በበጎ ፈቃደኝነት ሊገኝ ይችላል ወይ ? በትክክልስ ምን ላይ ይውላል ?
የህዝቧ ቁጥር 10 ሚሊዮን የሚደርሰው በምስራቅና መካከለኛው አፍሪቃ የምትገኘው ሩዋንዳ በህዝብ ብዛት ከተጨናነቁ የአፍሪቃ ሃገሮች አንዷ ናት ። ከህዝቧ ግማሽ ያህሉ ከድህነት ወለል በታች ነው የሚገኘው ። አብዛኛዎቹም የገጠር ነዋሪዎች ናቸው ። «አጋሲሮ »የተባለው የሩዋንዳ ልማት የገንዘብ ተቋም እነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች ለማገዝ ነው የተመሰረተው ። ባለፈው አመት በነሐሴ በሩዋንዳ መንግሥት የተቋቋመው ይሽው ድርጅት የመንገድ ሥራ ፕሮጀክቶችን በገንዘብ ይደግፋል ። ለዚህ ፕሮጀክት ድጎማ የሚያደርጉት እጎአ ከ1994 ቱ የሩዋንዳ የርስ በርስ ፍጅት በኋላ ከሃገር ተሰደው በአሁኑ ጊዜ በቤልጂግ በፈረንሳይ ወይም በካናዳ የሚኖሩ ብዙዎች የሩዋንዳ ተወላጆች ናቸው ። በሃገር ውስጥ ያሉ ሃገራቸውን መደገፍ የሚሹ ሩዋንዳውያንም ለዚህ ተቋም አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ በጀርመን የሩዋንዳ አምባሳደር ክርስቲን ንኩሊኪዪና ያስረዳሉ ።


« ይህ በበጎፈቃደኝነት የሚደረግ ነው ፤ እኛም በጎ ፈቃዱ ላይ ነው የምናተኩረው ። ከደሞዝ የሚቆረጥ ወይም እንደ ቀረጥ የሚታይ አይደለም ። ከዚያ ይልቅ እያንዳንዱ ሰው ምን ያህል እንደሚሰጥ ራሱ የሚወስንበት በበጎ ፈቃድ የሚደረግ መዋጮ ነው ። »
መዋጮው ሩዋንዳውያን ይበልጥ ሃላፊነት እንዲሰማቸውና በሀገራቸው እንዲተማመኑም የሚያደርግ ና የሚያጠነክራቸው ነው ። ሃሳቡ ተቀባይነት በማግኘቱም በመጀመሪያዎቹ 3 ወራት ተቋሙ 23 ሚሊዮን ዩሮ አግኝቷል ። 22 አመታት ጀርመን የኖሩት የሩዋንዳው ስደተኛ ፕሮቪደነ ቱዊሳብ ለተቋሙ ገንዘብ ካዋጡት አንዱ ናቸው ።
« ይህን የገንዘብ ተቋም በደንብ ነው የምደግፈው ። ምክንያቱም ተቋሙ ለሩዋንዳ የፋይናንስ ችግሮች ከመፍትሄም በላይ ነው ብዮ ስለማስብ ነው ። በሃገር ውስጥ እና በውጭ በሚኖሩ ሩዋንዳውያን ላይ አንድ አዲስ ሃሳብ ያጭራል ። ሁል ጊዜ በውጭ እርዳታ ከመመካት ይልቅ ራሳቸውን ችለው የወደፊትን መፃኤ እድል በራሳቸው እንዲወስኑ ያደርጋል ። »
በትጋት ከሚታየው መነሳሳት ጋር ገና ከጅምሩ በመዋጮ የማሰባሰቡ ዘመቻ ላይ ትችቶች እየተሰነዘሩ ነው ። መገናኛ ብዙሃን እንደሚሉት መዋጮው ሁልጊዜም በፈቃደኝነት አይደለም የሚሰጠው ። ሃብታም ሩዋንዳውያን ከገቢያቸው 10 በመቶ እንዲያዋጡ ይጠበቃል ። ከዚህ ሌላ በዚህ መዋጮ የማይሳተፉት የሚገጥማቸው ማህበራዊ ጫናም ከፍተኛ መሆኑን ታዛቢዎች የሚናገሩት ።

Dieses Foto wurde am 6. November 2009 in Cyangugu, Province de l'Ouest, Ruanda mit einer Canon PowerShot G10 aufgenommen.


« በአንዳንድ ጥቂት ሁኔታዎች መምህራንና ሌሎች ተራ ሠራተኞች ገንዘባቸውና ደሞዛቸው ካለፈቃዳችን ተቆረጠብን ሲሉ ያማርራሉ ። መንግሥትና ባለሥልጣናት እነዚህ ሰዎች በግድ ገንዘብ እንዲያዋጡ ከማድረግ ይልቅ በፈቃዳቸው መዋጮ እንዲሰጡ ማስተማሩ ላይ እንዲተኮር ያደርጋሉ ። »
ሩዋንዳ የውጭ እርዳታ ጥገኛ ናት ። ከበጀትዋ 40 በመቶው የሚሸፈነው ካደጉት አገራት በሚገኝ እርዳታ ነው ። ባለፈው ሐምሌ መጨረሻ ላይ የአውሮፓ ህብረት አሜሪካን ጀርመን ብሪታኒያ ኔዘርላንድስ ና ስዊድን ለሩዋንዳ ከሚሰጡት እርዳታ ከፊሉን አቋርጠዋል ። የዚህም ምክንያቱ በቅርቡ በወጣው

Virungas von Ruanda aus gesehen +++CC/John & Mel Kots+++, http://www.flickr.com/photos/melanieandjohn/397542294/ Lizenz:http://creativecommons.org/licenses/by-nc/2.0/deed.de aufgenommen am 24.1.2006, geladen am 25.10.2010

Virunga Mountains

የተመድ ዘገባ ሩዋንዳ በምሥራቅ ኮንጎ የሚንቀሳቀሰውን M23 በመባል የሚጠራውን የኮንጎ አማፅያን ቡድን ትደግፋለች በሚል ነው ። ዘገባው M23 ን ከበሰተጀርባ ሆነው የሚያንቀሳቅሱት የሩዋንዳ መከላከያ ሚኒስትር ጀምስ ካባርቤ ናቸው ሲልም አመልክቷል ። ሩዋንዳ ግን ክሶቹን አስተባብላለች ። ሩዋንዳ ከአሁኑ የገንዘብ ቅጣቱን እየተቀበለች ነው ። ትንሽቷ አገር ሩዋንዳ ከጀርመን ብቻ 21 ሚሊዮን ዩሮ አጥታለች ። ያም ሆኖ በጀርመን የሩዋንዳ አምባሳደር እንዳሉት የልማት ገንዘብ ማሰባሰቢያው ተቋም በተቋረጠው የውጭ እርዳታ ምክንያት የተጀመረ አይደለም ። የተቋሙን ገንዘብ አሁን የሚቆጣጠረው የሩዋንዳ የገንዘብ ሚኒስቴር ነው ። ይሄ ሃላፊነት በቅርቡ ለገልልተኛ አካል እንደሚሰጥ ተገልጿል

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic