የሩስያ ርዳታ እና የዩክሬይን ቅድመ ግዴታ | ዓለም | DW | 12.08.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የሩስያ ርዳታ እና የዩክሬይን ቅድመ ግዴታ

ዩክሬይን በሀገርዋ ምሥራቃዊ ከፊል በመንግሥቱ ጦር እና በዓማፅያን መካከል በቀጠለው ውጊያ ሰበብ የመሠረታዊ አቅርቦት ችግር ላጋጠመው ያካባቢው ነዋሪ ሩስያ በ280 የጭነት ተሽከርካሪዎች አጀብ ሰብዓዊ ርዳታ ልካለች፣

ይሁንና፣ ይኸው ርዳታ ለተቸገረው ሕዝብ የሚከፋፈልበትን አሰራር በተመለከተ ዩክሬይን የራሷን ቅድመ ግዴታ አስቀምጣለች። በቅድመ ግዴታው መሠረት፣ ርዳታው እንዲገባ የሚፈቀደው ርዳታው በድንበሩ ላይ ሲራገፍ እና በዓለም አቀፍ የቀይ መሥቀል ማኅበር ትብብር እንዲከፋፈል ሲደረግ ብቻ መሆኑን የዩክሬይን መንግሥት አስታውቋል። የሩስያ የጭነት ተሽከርካሪዎቹ አጀብ የሰብዓዊ ርዳታ ነው በሚል ላማፅያኑ ርዳታ ይዞ ሊገባ ይችላል በሚል ስጋት ነው ዩክሬይን ይህን ቅድመ ግዴታ ያቀረበችው።

ዣኔት ዛይፈርት

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic