የሩሲያ ጋዝ ወደ ጀርመን የሚፈስበት ቧምቧ ዉዝግብ እልባት አገኘ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 08.02.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የሩሲያ ጋዝ ወደ ጀርመን የሚፈስበት ቧምቧ ዉዝግብ እልባት አገኘ

የሩሲያ ጋዝ ወደ ጀርመን የሚፈስበት ቧምቧን በመዘርጋት፣መከታተልና መቆጣጠር ሰበብ በአዉሮጳ ሕብረት አባል መንግሥታት መካከል ተፈጥሮ የነበረዉ አለመግባባት ተወገደ።ከሩሲያ ወደ ጀርመን ከዚያም ወደ ሌሎች የአዉሮጳ ሐገራት ጋዝ የሚከፋፈልበትን ቧምቧ የመዘርጋቱ ዉል የሕብረቱን አባል መንግስታት በተለይም ጀርመንና ፈረንሳይን ሲያወዛግብ ነበር።

የሩሲያ ጋዝ ወደ ጀርመን የሚፈስበት ቧምቧን በመዘርጋት፣መከታተልና መቆጣጠር ሰበብ በአዉሮጳ ሕብረት አባል መንግሥታት መካከል ተፈጥሮ የነበረዉ አለመግባባት ተወገደ።ከሩሲያ ወደ ጀርመን ከዚያም ወደ ሌሎች የአዉሮጳ ሐገራት ጋዝ የሚከፋፈልበትን ቧምቧ የመዘርጋቱ ዉል የሕብረቱን አባል መንግስታት በተለይም ጀርመንና ፈረንሳይን ሲያወዛግብ ነበር። ዉዝግቡን ለማስወገድ የአባል መንግስታት ተወካዮች በተከታታይ ሲደራደሩ ነበር።

የጀርመንዋ መራሒተ መንግስት ወይዘሮ አንጌላ ሜርክል ዛሬ እንዳስታወቁት ፈረንሳይና ጀርመን በመስማማታቸዉ ዉዝግቡ ተወግዷል።«የጋዙን መመሪያ በተመለከተ ከስምምነት ላይ ደርሰናል።ስምምነት ማድረግ የተቻለዉ ጀርመን ፈረንሳይ በቅርብ ተባብረዉ በመስራታቸዉ ነዉ።ጀርመን ከተለያዩ ምንጮች ኃይል የማግኘት መብቷን ማስከበር ትፈልጋለች።ሩሲያ ከነዚሕ ምንጮች አንዷ ናት።ብቸኛዋ ግን አይደለችም።እዚሑ ጀርመን ዉስጥም ፈሳሽ ጋዝ እናጠራቅማለን።»
አዲስ በተደረገዉ ስምምነት መሠረት ቦልቲክን አቋርጦ ጀርመን የሚደርሰዉን የጋዝ ቧምቧ የሚያስተዳድረዉ የሩሲያዉ ኩባንያ ጋዝፕሮም ለአዉሮጳ ሕብረት መመሪያና ደንቦች ተገዢ ነዉ።የአዉሮጳ ሕብረት ምክር ቤት ወደፊት በሚወስነዉ መሰረት የስምምነቱ ዝርዝር አፈፃፀም ይፋ ይሆናል።

 

ነጋሽ መሐመድ 

አዜብ ታደሰ