የረጲየቆሻሻ ክምር አደጋና የአዲስ አበባ ዉሎ | ኢትዮጵያ | DW | 14.03.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የረጲየቆሻሻ ክምር አደጋና የአዲስ አበባ ዉሎ

ባለፈዉ ቅዳሜ ማታ ከተደረመሰዉ የአዲስ አበባ የቁሻሻ ክምር መሐል አንዲት ሴት በሕይወት ተገኙ።የፈረንሳዩ ዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ የአዲስ አበባ ከተማ ባለሥልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበዉ ሴትዮዋ ከቁሻሻዉ ክምር መሐል የወጡት ዛሬ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 05:32

የረጲየቆሻሻ ክምር አደጋና የአዲስ አበባ ዉሎ

በሌላ በኩል የሟቾች ቁጥር መጨመሩን የሚገልፁ ዘገባዎች የተለያዩ የሟቾች ቁጥርን እየጠቀሱ እየዘገቡ ነዉ።  እስካሁን ባለን መረጃ መሰረት ከሆነ የሟቾች ቁጥር 82 ደርሶአል። መንግሥትም በሃገሪቱ የሦስት ቀናት የብሔራዊ ሃዘን ቀንን አዉጅዋል። ትናንት ባገኘነዉ ዘገባ መሰረት ከሟቾች መካከል 15 ቱ ሕጻናት መሆናቸዉን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቦአል።  የረጲ የቆሻሻ መጣያ ስፍራ አካባቢ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደሚኖሩ የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ ቃል አቀባይ አቶ አማረ መኮንን፤ በቆሻሻዉ ማጠራቀምያ ቦታ ሰዎች የሚበላ ምግብንና  የሚጠቅም እቃን ይፈልጉ እንደነበር ለሮይተርስ ተናግረዋል። በቆሻሻዉ ቁልል የተቀበሩትን ሕይወት ለማትረፍ ፍለጋዉ እንደቀጠለና 54 ሠዎች ከአደጋዉ ተርፈዉ በሆስፒታል ክትትል እንደተደረገላቸዉ ቃል አቀባዩ ለዜና አዉታሩ ገልፀዋል። ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ የአዲስ አበባ ከተማ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በበኩላቸዉ በክረምት ወራት ይህን አይነቱን አደጋ ለመታደግ ጥንቃቄ ይደረግ እንደነበረና  አሁን በጋ ላይ አደጋዉ መከሰቱ ድንገተኛ መሆኑን ገልፀዋል። አካባቢዉ ላይ ይኖሩ የነበሩ ወደ 300 የሚሆኑ ሰዎች ወደ ሌላ ማቆያ ቦታ መወሰዳቸዉንም ተናግረዋል። ሊዘጋ ነዉ ሲባል የነበረዉ የረጲ የቆሻሻ ማጠራቀምያ ቦታ በኦመት 300 ሺህ ቶን ቆሻሻ ይጣልበታል።  ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት የአዲስ አበባዉን ወኪላችንን ስለ ዛሬዉ ዉሎ ስለሚሰማዉ አስተያየትና ስለማኅበረሰቡ ጉዳይ በስልክ ጠይቀነዉ ነበር። 

ዮኃንስ ገብረግዚአብሔር 

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic