ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የኤርትራና የአማራ ኃይላት ወዳጅነትና የወዳጅነቱ ደረጃ ለጊዜ ሒደት የሚተዉ ነዉ።የኢትዮጵያ ፈደራዊ መንግስት «የክልሎች ልዩ ኃይላትን ዳግም ለማደራጀት» ባለዉ ዘመቻ የአማራ ታጣዊዎችን ትጥቅ ማስፈታት ከጀመረበት ካለፈዉ ወር ወዲሕ ግን በመንግስትና በአማራ ኃይላት መካከል የተፈጠረዉ ጠብ እየተካረረ መምጣቱን ለማወቅ አስተንታኝ አያስፈልግም።
የኢትዮጵያ መንግስት በአማራ ክልል የናረዉን ዉጥረት ለማስተንፈስ በኃይልም፣በዛችም፣በሕግም እየተጫነ፣ ኦሮሚያ ዉስጥ ከሸመቀዉ ከኦሮሞ ነፃ አዉጪ ሰራዊት (ኦነሰ) ጋር ድርድር ጀምሯል
የአውሮጳ ኅብረት የተቋረጠውን የበጀት ድጋፍ ለኢትዮጵያ መንግሥት የሚሰጠዉ የሻከረው ግንኙነት ወደ ነበረበት ሲመለስ እንደሆነ የኅብረቱ ቃል አቀባይ ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል። ኅብረቱ የልማት ዕርዳታ የሚሰጥበትን "መልቲ አንዋል ኢንዲኬቲቭ ፕሮግራም" በግጭት ማቆም ሥምምነቱ "ዘላቂ አተገባበር መሠረት" ዳግም ለመጀመር ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።
የትናንቱ የድምፅ አሰጣጥ ሒደት በተወሰኑ አካባቢዎች ካጋጠሙ መለስተኛ ችግሮች በስተቀር በታቀደው መሠረት መደረጉን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡