የረሃብ አድማ እንደ ፖለቲካዊ መሣሪያ፣ | ዓለም | DW | 20.09.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የረሃብ አድማ እንደ ፖለቲካዊ መሣሪያ፣

ከ 80 ዓመት በፊት ፤ በዛሬዋ ዕለት ፣ እውቁ የሰላማዊ ትግል ፈላስፋ ማህተመ ጋንዲ፤ በእሥራት ላይ እንዳለ ፣ የሚላስ የሚቀመስ ወደ አፉ ላያስጠጋ ፣ ሞት ነፍስና ሥጋውን እስኪለይ ለመጾም በይፋ አሳወቀ። ራስን ማስራብ ፣ የፖለቲካ መሳሪያ ሆኖ

default

እንደሚያገለግል፤ ዓለም ከእርሱ ተማረ። በዛሬዋ ህንድም ቢሆን፤ የረሃብ አድማ የፖለቲካ ሙግት መግጠሚያ መሣሪያ መሆኑ አልቀረም።

የሚታወቀው ሞሃንዳስ ካራምቻንድ ጋንዲ በሚል ስም ነው። «ማሃታማ» (ትልቅ ነፍስ)የሚለውን ማዕረግ መሰል ስም ከፊት የጨመረለት፣ የእርሱን ፍልስፍና ይከተሉ ከነበሩ አድናቂዎቹ መካከል አንዱ ነው። በረሃብ ሞጌው የወጣ መስሎ ይታይ የነበረው አጭሩና ባጣም ቀጭኑ ሰው ጋንዲ፤እ ጎ አ በ 1948 ዓ ም በሰው እጅ ህይወቱ እስከጠፋችበት ዕለት ድረስ ፤ ያኔ በህንድ እንደተዘረጋ የነበረውን የባሪታንያ የቅኝ አገዛዝ ሥርዓት ሲታገል የነበረ ሰው ነው። ቅኝ ገዥዎቹ የብሪታንያ ባለሥልጣናትም የትግሉን ሂደት እስከ ውጤቱ እንዲገነዘቡትም ሆነ እንዲያዩት አብቅቷል።

Indien Khan Abdul Ghaffar Khan Mahatma Gandhi

«ራሴን («የሰላም ወታደር »)አድርጌ እቆጥራለሁ፤ ዲስፕሊን ያለውና እውነትን ለመተግበር ቃል የገባ!»

እ ጎ አ መስከረም 20 ቀን 1932 ዓ ም፤ ጋንዲ ፣ እስከ ዕለተ ሞቱ የዘለቀውን የመጀመሪያውን የረሃብ አድማ ጀመረ። ጋንዲ በዚህ እርምጃው ፣ እንግሊዞች የምርጫ መብትን በዘር ፣ በጎሳ እንዳይከፋፍሉ ለማስቆም ነበረ የፈለገው። በጎሣ ፤ በዘር መከፋፈሉ ፣ የህንድን ኅብረተሰብ ይከፋፍላል፤ ያዳክማል የሚል ሥጋት ነበረውና!ጋንዲ 4 ቀንና ሌሊት የረሃብ አድማ ከመታ በኋላ ገላጋይ ስምምነት ላይ ተደረሰ። ይህን በተመለከተም ያኔ እንዲህ ማለቱ የሚታወስ ነው።

Indien Mahatma Ghandi Ehrung in Neu Delhi

« እጅግ አስተማማኙ መንገድ በዘመናዊው የህግ የበላይነት ማመን ነው። የሐቅና የፍቅር ህግ በሆነው--እምነት ያለው ሰው፤ ማናንኛቸውንም ከሐቅና ከፍቅር ጋር የማይስማሙ፤ የሚጻረሩ ነገሮችን መቋቋም ይችላል። »

ጋንዲ የጀመረው የረሃብ አድማ፤ በአንድ ጊዜ ብቻ አልተገታም። ጾም ፤ ጸሎትና የሲብል አመጽ(እምቢተኝነት)የዕለት ተለት መርኀ ግብሩ ሆነ። ማህተማ ጋንዲ፤ ያላንዳች መታከት፣ የመራው በሰላማዊ መንገድ ያካሄደው የተቃውሞ እርምጃ፤ ህንድ ነጻነቷን እንድትቀዳጅ አብቅቷል። ለዚህም ነው እስከዛሬ ድረስ የህንድ የነጻነት አባት እየተባለ በክብር የሚታወሰው። አና ሃዛር የተባሉት የማኅበራዊ ፍትኅ ታጋይ ፣ ጋን ዲን አርማ በማድረግ ነው የተነሳሱት።

የሃዛር ንቅናቄ በህንድ በተስፋፋው ሙስና ላይ ነው ያነጣጠረው። በረሃብ አድማ ፣ ፓርላማው ብርቱ ህግጋትን እንዲያወጣ ማስገደድ ተገቢ ነው የሚል እምነት አለው። የፖለቲካና የማኅበራዊ ኑሮ ምሁር ፣ አዲቲያ ኒጋም፣ በአና ሃዛር ንቅናቄና በመሠረታዊው የጋንዲ ፍልስፍና ትልቅ ልዩነት አለ ባይ ናቸው።

Indien Mahatma Ghandi Ehrung in Bombay

« ጋንዲ በፖለቲካ ንግግሩ ፍቅርን ያስገባ ነበር። የረሃብ አድማው፤ የወገን ፍቅር መግለጫ ነበር። ጾም አንዱ የፖለቲካ መደራደራያ መሳሪያውና የሞራል ብቃቱ ምልክት ነበረ። ጋንዲ የተሣካለት ይቅርታ አድራጊም ስለነበረ ነው። የአና ሃዛር የተለየ ነው። ከረሃብ አድማና ተቃውሞ በስተቀር ፤ ሌላ ምንም የለም። »

ዲስፕሊንን መሠረት ባደረገ የህይወት አመራር የታወቁ ናቸው የሚባሉት ራሃዳ ብሃት የተባሉት የጋንዲ የሰላም ድርጅት ባልደረባ፣ በዘመናዊቷና እኩልነት በጠፋባት ፤ በድሃውና በሃብታሙ ያለው ልዩነት እጅግ በሰፋባት ህንድ ፣ ምነው የላቀ የማህተማ ጋንዲ መንፈስ በሰፈነ ! ይላሉ።

« ጋንዲ ፖለቲከኛ አልነበረም፤ ትምህርቱ ሁሉንም የሚያቅፍ ፤ አገልግሎቱም ለህዝብ ነበር። ዛሬ ዓለምን በኅሊና መነጽር ስመለከታት ጋንዲ ከምንጊዜውም በበለጠ አሁን ያስፈልግ እንደነበረ ይሰማኛል።»

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 20.09.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/16C5g
 • ቀን 20.09.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/16C5g