የረሃብ አደጋ ስጋት በኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 04.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የረሃብ አደጋ ስጋት በኢትዮጵያ

ሁለት ሦስተኛዉ ዜጋ በረሃብ አደጋ ላይ ነዉ ከተባሉት ስምንት ሃገራት መካከል  የመን፤ ኢትዮጵያ ፣  ሱዳን፤  ዴሞክራቲክ ኮንጎ፣ ሶርያ ይገኙበታል። እንዲያም ሆኖ በከፍተኛ የረሃብ አደጋ እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንዲኖሩ የተገደዱ ሕጻናት ጉዳይ አሁንም ቢሆን አሳሳቢ መሆኑን አበክሮ ገልፆአል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:29

የመን፤ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን፤ ዴሞክራቲክ ኮንጎ፣ ሶርያ በረሃብ አደጋ ላይ ናቸዉ

ከ 113 ሚሊዮን የሚበልጥ ሕዝብ በጦርነት እና በተከሰተ የተፈጥሮ አደጋ « ለአስከፊ ረሃብ»  መጋለጡን የተመድ አሳታወቀ። ድርጅቱ ባለፈዉ የጎርጎረሳዉያን 2018 ዓመት በ 53 የዓለም ሃገራት ያደረገዉን ጥናት በዚህ ሳምንት ይፋ ሲያደር እንደገለፀዉ ለረሃብ አደጋ የተጋለጠዉ አብዛኛዉ ሕዝብ የሚገኘዉ በአፍሪቃ ሃገራት ዉስጥ ነዉ። እንድያም ሆኖ የረሃብተኛዉ ቁጥር ቀደም ካሉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር ቁጥሩ በጥቂቱም ቢሆን መቀነሱን የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት «FAO» ገልፆአል። ሁለት ሦስተኛዉ ዜጋ በረሃብ አደጋ ላይ ነዉ ከተባሉት ስምንት ሃገራት መካከል  የመን፤ ኢትዮጵያ ፣  ሱዳን፤  ዴሞክራቲክ ኮንጎ፣ ሶርያ ይገኙበታል። የዓለም የእርሻ ድርጅት «FAO» እንዲያም ሆኖ በከፍተኛ የረሃብ አደጋ እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንዲኖሩ የተገደዱ ሕጻናት ጉዳይ አሁንም ቢሆን አሳሳቢ መሆኑን አበክሮ ገልፆአል። የዋሽንግተን ዲሲዉ ወሊላችን መክብብ ሸዋ በኢትዮጵያ የሚታየዉን የረሃብ አደጋ ለመከላከል ግጭትን ማስወገድ የመስኖ ርሻን ማስፋፋት እንዲሁም የመሬትን የግል ባለቤትነት ማረጋገጥ እንደሆነ የተናገሩ ምሁርን አነጋግሮ ዘገባ ልኮልናል። 


መክብብ ሸዋ 


አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ 

Audios and videos on the topic