የሦስትዮሹ የህዳሴ ግድብ ቴክኒክ ኮሚቴና አማካሪዎች ውዝግብ | አፍሪቃ | DW | 12.11.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የሦስትዮሹ የህዳሴ ግድብ ቴክኒክ ኮሚቴና አማካሪዎች ውዝግብ

ላለፈዉ ስድስት ወራት የህዳሴ ግድብ በመባል የሚታወቀዉ እንዲያጠኑ የፈረንሣዩ «ቢአርኤል» እና የኔዝርላንዱ «ዴልታሬስ» የአማካሪ ኩባኒያዎች መሃል የተፈጠረዉን ኣለመግባባት ካልተፈታ ከሌሎች አመራጮች ዳግም ጨረታ ማዉጣት እንደሚጠበቅባቸዉ በዉሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሙያ ለዶቼ ቬሌ ተናግሮዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:05
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:05 ደቂቃ

ሶስትዮሹ የህዳሴ ግድብ የቴክኒክ ኮምቴ

ባለፈዉ ሳምንት በካይሮ ለሁለት ቀናት የተካሄደዉ የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን የጋራ የቴክኒክ ኮሚቴ ስብሰባ በሁለቱ አማካሪ ኩባንያዎች መሃል የተፈጠረዉን አለመግባባት ለመፊታት ቢሞክሩም መፍትሄ ሳይገኝ ተለያይተዋል። በዉሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚንስቴር የወሰን ተሻጋር ወንዞች ጉዳይ ዳይሬክተር ኢንጂነር ተሾመ አጥናፌ ስያብራሩ፣ «ወደ ቀጣዩ አማራጭ ከመሄዳችን በፊት ለመጨረሻ ጊዜ እነኝህ ሁለቱን አማካሪዎች በተገኙበት የሶስትዮሽ ብሄራዊ ኮሚቴ አባላትና የዉሃ ሚኒስትሮች ባሉበት የመጨረሻዉን ጥረት በሕዳር መጨረሻ ሳምንት ላይ ሱዳን ካርቱም አድርገን የሚግባቡበት መንገድ ካለ ስራዉን ልናስቀጥል፣ የማይሆን ከሆነ ግን ሌሎች አማራጮችን እንድንወስን ለመጨረሻ ጊዜ እነኝህን አማካሪዎች ተጠርቶ ኮሚቴ ፊት ቀርቦ ሃሳባቸዉን እንዲያቀርቡ ቀጠሮ ይዘን ነዉ የተለያየነዉ።»


ሦስቱ አገሮች በዚህ ወር መጨረሻ ካርቱም ሲገናኙ ስድስት ወራት የዘለቀውን ልዩነት ለመለየትና ለመፍታት አቅደዋል። ልዩነቱን መፍታት ካልተቻለ አንደኛው አማካሪ ስራውን እንዲቀጥል ማድረግ አሊያም ጨረታው በድጋሚ ሊወጣ እንደሚችል አቶ ተሾመ አጥናፌ እንዲህ ይላሉ፣

«በሌላ በኩል እንደገና መመለስ አይሆንም ሆይ ለተባለዉ፣ እንግዲህ በጨረታ ሂደት ዉስጥ የጨረታ ህግና ደንብ አለ፣ በሶስቱም ሃገሮች የተለያየ የጨረታ ህግና ደንብ ቢኖርም፣ በዋናነት ግን የዓለማቀፍ አሰራር ስለምንከተል እነኝህ ሁለቱ አማካሪዎች ወይም ከዚህ በፊት የተወዳደሩት አማካሪዎች ለዚህ ስራ ምቹ አይደለም ወይም ከስምምነት የማንደርስ ከሆነ ተመልሶ ጨረታ ይወጣል። ጨረታዉ መፋጠን ያለበት ብዙ አመራጮች አሉ፣ ጨረታ አንደኛዉ በግልፅ ጨረታ፣ ሁለተኛዉ የተመረጡ ኩባንያዎች በመጋበዝ አለ። ሶስተኛዉ በቀጥታ የሚሰጥበትም መንገድ ስላለ ወደፊት እነኝህን አማካሪዎች ጋር ደጋግመን ያለዉን ችግር መፍታት ከሞከረን በኋላ ስራዉን ለማፋጠን የትኛዉ የግዥ ዘዴ ጥሩ ነዉ የሚለዉን መርጠን ቶሎ የምንሄድበትን እናደርጋለን፣ ግን ወደኋላ ተመልሰን መስራታችን የማይቀር ነዉ ማለት ነዉ።»


በኢትዮጵያ፣ግብፅ እና ሱዳን የተቋቋ የህዳሴ ግድብ የጋራ የቴክኒክ ኮሚቴ ግድቡን እንድያጠኑ ብረለ ና ዴልታሬስ አማካሪ ኩባንያዎችንች መምረጣቸዉ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ዴልታረስ የተሰኘዉ ኩባንያ የፕሮጀክቱ 30 በመቶ እንድይዝ ተወስኖለት እንደነበረ ቢታወቅም፣ ራሱን ከጥናት ሥራው ማግለሉን በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ በደረ-ገጹ አስታውቋል። የተቋረጠበት ምክንያት ግልፅ ባይሆንም እስከሁን ሁለቱም ኩባንያዎች ሳይስማሙ ቀጥለዋል። ኢትዮጵያ ስምምነቱ ለመጓተቱ ከተጠያቂነት ለመዉጣት የቴክኒካል ጥናት እያካሄደች መሆኑን አቶ ሞቱማ ማቃሳን ጠቅሰው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ባለፈው ሚያዝያ ወር ሶስቱ አገሮች ኢትዮጵያ የምትገነባው የታላቁ የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ „declaration of principles“ የተሰኘ ስምምነት ሱዳን ካርቱም ላይ መፈራረማቸው አይዘነጋም።


መርጋ ዮናስ


አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች