የሠብአዊ መብት ዕለትና ኢትዮጵያዉን ሠልፈኞች | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 10.12.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የሠብአዊ መብት ዕለትና ኢትዮጵያዉን ሠልፈኞች

የሠዉ ልጆች መሠረታዊ ሠብአዊ መብት እንዲከበር የሚደነግገዉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ደንብ (ቻርተር) የፀደቀበት 62ኛ አመት ዛሬ በመላዉ አለም በተለያዩ ሥነ-ሥርዓቶች እየታሰበ ነዉ።

default

የጀርመን ምክር ቤት

እዚሕ ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ሠብአዊ መብት ያከብር ዘንድ የጀርመን መንግሥት ግፊት እንዲያደርግበት በርሊን ዉስጥ ባደረጉት ሠልፍ ጠይቀዋል። በጀርመን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ያስተባበረዉ ሠልፈኛ ጥያቄዉን ለጀርመን መራሒተ-መንግሥትና ለዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ፅሕፈት ቤቶች አቅርቧል። የሠልፉን ሒደት የተከታተለዉን የበርሊኑን ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤልንና ከሰልፉ አስተባባሪዎች አንዷን ነጋሽ መሐመድ በስልክ አነጋግሯቸዋል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ