የሠራተኞች  አድማ በኮይሻ ኃይል ማመንጫ | ኤኮኖሚ | DW | 19.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኤኮኖሚ

የሠራተኞች  አድማ በኮይሻ ኃይል ማመንጫ

ከአምስት  ሺህ በላይ የሚሆኑ  የኮይሻ ሃይል ማመንጫ ግድብ ሠራተኞች  የሥራ ማቆም አድማ ከመቱ አንድ ሳምንት ሆናቸው።  በግድቡ ፕሮጀክት የሥራ ኃላፊዎች  ተፈድሞብናል  የሚሉት  የአስተዳደር በደል ፣ ሙስና እና  የመብት ጥሰቶች  የአድማው  መነሾ  ምክንያት  ናችው  ተብሏል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:35

«የፕሮጀክቱ አመራሮች ከሠራተኞች ጋር ድርድር በማድረግ ላይ ናቸው»

  ከአካባቢው የሚውጡ  መረጃዎች  እንሚያመለቱት  በአሁኑ ወቅት   ማቆም  አድማው  ምክንያት ይል ማመንጫ  ግድብ  ግንባታ  ሙሉ  በሙሉ  እንደተቋረጠ  ይገኛል። ከአካባቢው የሚውጡ መረጃዎች እንዳሚያመለከቱት በሥራ ማቆም አድማው ምክንያት የኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታው አሁንም ሙሉ በሙሉ እንደተቋረጠ ይገኛል። በአሁኑ ውቅትም  የፕሮጀክቱ አመራሮች ከሠራተኞቹ ጋር ድርድር  በማካሄድ ላይ እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል።

ዘግይቶ  በደረሰን  ዜና ደግሞ  ሠራተኞቹ  ዛሬ ሲያደረጉት የነበረውን ድርድር  አሁን ማምሻወን በማጠናቀቅ ከነገ  ቅዳሜ ጀምሮ  ወደሥስራ  ገበታቸው ለመመለስ  ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። ሠራተኞቹ ከስምምነት ላይ ሊደርሱ የቻሉት የአስተዳደር በደል ፈድመዋል በሚል ቅሬታ ሲነሳባቸው ከነበሩት   የፕሮጅክቱ  የሥራ ሃላፊዎች  መካከል ሁለቱ ከሥራቸው በመታገዳቸው መሆኑም ተሰምቷል። የዲ ደብሊው ታማኝ ምንጮች እንዳረጋገጡት እገዳ የተጣለባቸው ሁለቱ ሃላፊዎች የግድቡን ግንባታ በኮንትራት እያከናወነ  በሚገኘውና  ሳሊኒ በተባለው ኩባንያ ወስጥ በከፍተኛ  የሰው ሀብትና የፋይናንስ  ኃላፊነት ቦታዎች በማገልገል የነበሩ መሆናችው ታውቋል።  

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic