የሠራተኞች ተቃውሞ በአውሮፓ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 15.11.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የሠራተኞች ተቃውሞ በአውሮፓ

በአሁኑ ጊዜ መንግሥታት የቁጠባ መርሃ ግብሩን መቀጠሉን ሲመርጡ ተቃዋሚዎች ደግሞ አሁን የተያዘውን መንገድ በመተው ሥራ አጥነትን ሊቀንስ የሚችልና ማህበራዊ ዋስትና የሚያጠናክር እርምጃ እንዲወሰድ እየጠየቁ ነው ። ተንታኞች እንደሚሉት ተቃውሞ የበረታበት የቁጠባ መርሃ ግብር ከቀጠለ በአውሮፓ ማህበራዊ ቀውስና አለመረጋጋት ሊያስከትል ይችላል ።

የበርካታ የአውሮፓ ሃገራት ሠራተኖች ትናንት በተካሄዱ ሰልፎችና ና የሥራ ማቆም አድማዎች በየሃገራቸው የሚካሄዱ የቁጠባ እርምጃዎችን ሲቃወሙ ውለው አምሽተዋል ።  በአሁኑ ጊዜ መንግሥታት የቁጠባ መርሃ ግብሩን መቀጠሉን ሲመርጡ ተቃዋሚዎች ደግሞ አሁን የተያዘው መንገድ በመተው ሥራ አጥነትን ሊቀንስ የሚችልና ማህበራዊ ዋስትና የሚያጠናክር እርምጃ እንዲወሰድ እየጠየቁ ነው ። ተንታኞች እንደሚሉት ተቃውሞ የበረታበት የቁጠባ መርሃ ግብር  ከቀጠለ በአውሮፓ ማህበራዊ ቀውስና አለመረጋጋት ሊያስከትል ይችላል ። የብራሰልሱን ዘጋቢያችንን ገበያው ንጉሴን ስለ ተቃውሞው ስለ መንግሥታቱ እርምጃና መፍትሄው ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ ። ገበያው ትናንት የተካሄዱትን ተቃውሞዎች ስፋት በማብራራት ይጀምራል ። 

ገበያው ንጉሴ

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic