የሟቹ ረዳት አብራሪ አህመድ ኑር ጓደኞች | ኢትዮጵያ | DW | 14.03.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የሟቹ ረዳት አብራሪ አህመድ ኑር ጓደኞች

እሁድ ለጉዞ ከተነሳ ብዙም ሳይቆይ የወደቀው ኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የበረራ ባለሙያዎችም ሆኑ ተሳፋሪዎቹ ላይ የደረሰው ድንገተኛ ሞት ዛሬም ሀዘኑ አልወጣም። የቦይንግ 737 ማክስ 8 ረዳት አብራሪ አህመድ ኑር መሐመድ ጓደኞች ስለወጣቱ የበረራ ባለሙያ የሚያውቁትን ለDW ገልጸዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:02

«አህመድ ኑር ማንበር የሚወድ ረጋ ያለ ወጣት ነበር»

 በቦይንግ 737 ማክስ 8 ተሳፍረው የነበሩ መንገደኞች ቤተሰቦችም ሆኑ የበረራ ባለሙያዎቹ ዘመድ ወዳጆች ከደረሰው አደጋ የተነሳ አስከሬን መቅበር ባለመቻላቸው የቻሉት አደጋው ከደረሰበት ስፍራ በመሄድ እርማቸውን ለማውጣት መሞከራቸው ይሰማል። በዕለቱ የቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን 30 ዓመት ባልሞላቸው ወጣት አብራሪዎች ነበር ካሰበት ሊደርስ የተነሳው፤ ከመንገድ ቀረ እንጂ። ረዳት አብራሪውን አህመድ ኑር መሃመድን በቅርብ የሚያውቁት የ26 ዓመቱን  የአውሮፕላን አብራሪ ማንበብ የሚወድ ረጋ ያለ ወጣት እንደበር ለDW ገልጸዋል። ከአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ ዘገባ ልኮልናል።

ሰሎሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ

Audios and videos on the topic