የሟሟያ ምርጫ በኢትዮዽያ | ኢትዮጵያ | DW | 09.02.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሟሟያ ምርጫ በኢትዮዽያ

በኢትዮዽያ በመጪው የካቲት ወር መጨረሻ ላይ የሟሟያ ምርጫ ይካሄዳል። በዚህ ምርጫ ተቃዋሚዎች አይሳተፉም። ምርጫ ቦርድ ይህ የኔ ችግር አይደለም ይላል።

default

ኢትዮዽያ ባለፈው 4ኛውን ብሄራዊ ምርጫ ካደረገች፤ ገዢው ፓርቲ 99.6 በመቶ የምክር ቤት መቀመጪዎችን ካሸነፈና አዲሱ ምክር ቤት ከተቋቋመ ከ5 ወር ገደማ በኋላ ምርጫ ቦርድ ለሟሟያ ምርጫ እየተሰናዳ ነው። የካቲት መጨረሻ ላይ በሶስት ክልሎች ይኸው የሟሟያ ምርጫ ይደረጋል። ይሁንና ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫው እንደማይሳተፉ ገልጸዋል። ምርጫ ቦርድ የምዝገባ ጊዜውን በአንድ ሳምንት አራዝሟል። መሳይ መኮንን የምርጫ ቦርድ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊንና የኢዴፓ ፕሬዝዳንት አቶ ልደቱ አያሌውን በማነጋገር ያዘጋጀው ዘገባ ቀጥልሎ ይቀርባል።

የሟሟያ ምርጫው በአዲስ አበባ፤ በኦሮሚያና በደቡብ ክልሎች ይካሄዳል። የተወካዮች ምክር ቤትንና የየክልሎቹን ምክር ቤቶች መቀመጪያዎችን ጠቅልሎ ያሸነፈውና ገዢው ፓርቲና ሁለት ሌሎች ፓርቲዎች  የሚወዳደሩበት ይህ የሟሟያ ምርጫ በያዝነው ወር መጨረሻ ላይ ቢካሄድም በህዝቡም ሆነ በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ትኩረት አልተሰጠውም። ወይዘሮ የሺ ፈቃደ በኢትዮዽያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ ሃላፊም በእርግጥ በዚህ አስተያየት ይስማማሉ።

በዚህ የሟሟያ ምርጫ ላይ በመራጭነት ለሚመዘገቡት የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶ ምዝገባው ቢጀመርም እንደተፈለገውና እንደተጠበቀው አልሆነም። የመራጮች አነስተኛ ሆኖ ተገኝቷል። በሟሟያ ምርጫው የሚሳተፉ ፓርቲዎች ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት በሚል ቦርዱ ባለፈው ሃሙስ የምዝገባውን ጊዜ በአንድ ሳምንት ማራዘሙን አስታውቋል። የቦርዱ የህዝብ ግኑኝነት ማስተባበሪያ ሃላፊ ወይዘሮ የሺ ፈቃደ የሟሟያ ምርጫ ቧሟሆኑ እንጂ ተቃዋሚዎች ባለመኖራቸው የተፈጠረ አይደለም ይሉታል።

በእርግጥ ከሶስት ሳምንት በኋላ ለሚካሄደው ምርጫ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትኩረት አልሰጡም። የስምንት ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው መድረክና የመላው ኢትዮዽያ አንድነት ድርጅት መኢአድ በዚህ ምርጫ እንደማይሳተፉ የገለጹት ቀደም ብለው ነው። የኢትዮዽያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ኢዴፓም በምርጫው እንደማይሳተፍ ነው ፕሬዝዳንቱ አቶ ልደቱ አያሌው የሚገልጹት።