የ«ሞት በኩላሊት ይብቃ» እና የስኳር ህሙማን ማህበራት ጥሪ | ኢትዮጵያ | DW | 09.11.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የ«ሞት በኩላሊት ይብቃ» እና የስኳር ህሙማን ማህበራት ጥሪ

« ሞት በኩላሊት ይብቃ» የተባለው የኩላሊት ህሙማን ማህበር ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ ባዘጋጀው የእግር ጉዞ ላይ የኩላሊት ህክምና የሚያስፈልገው ወጭ ከፍተኛ በመሆኑ መንግሥት የማከሚያ መሣሪዎች በነፃ እንዲገቡ እንዲፈቅድ ጥሪ አቅርቧል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:29
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:29 ደቂቃ

የሁለት ማህበራት ጥሪ

የኩላሊት ህክምና መሣሪያዎችና ለህክምናው የሚያስፈልጉ መድሀኒቶች ከቀረጥ ነፃ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ተጠየቀ ።« ሞት በኩላሊት ይብቃ» የተባለው የኩላሊት ህሙማን ማህበር ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ ባዘጋጀው የእግር ጉዞ ላይ የኩላሊት ህክምና የሚያስፈልገው ወጭ ከፍተኛ በመሆኑ መንግሥት የማከሚያ መሣሪዎች በነፃ እንዲገቡ እንዲፈቅድ ጥሪ አቅርቧል። የኢትዮጵያ የስኳር ህሙማን ማህበር፣ ትናንት ባከሄደው ተመሳሳይ የእግር ጉዞ የስኳር በሽታን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት መንግሥት እና ህብረተሰቡ ከጎኑ እንዲቆሙ ጥሪ አስተላልፏል። ሁለቱንም ጉዞዎች የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic