የሞሪታንያ ፕሬዚደንት ተተኩሶባቸው ቆሰሉ | አፍሪቃ | DW | 14.10.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የሞሪታንያ ፕሬዚደንት ተተኩሶባቸው ቆሰሉ

የሞሪታንያ ፕሬዚደንት ኡልድ አብደል አዚዝ ትናንት በመዲናይቱ ኑዋክሾት በአጀብ እየተጓዙ ሳለ ወታደሮች የፕሬዚደንቱ አጀብ መሆኑን ካለማወቅ በከፈቱት ተኩስ እጃቸው ላይ ከቆሰሉ በኋላ ዛሬ ለሕክምና ወደ ፓሪስ ፈረንሳይ መሄዳቸው ተነገረ።በዚያ ከተደረገላቸው ቀዶ ጥገና በኋላ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ፕሬዚደንቱ ለሕዝባቸው ከፓሪስ ሐኪም ቤት አልጋቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።  ፕሬዚደንት አብደል አዚዝ የደረሰባቸው የመቁሰል አደጋ ለሕይወታቸው አስጊ አለመሆኑን የሀገሪቱ መገናኛ ሚንስትርም በቴሌቪዥን ገልጸዋል። ሚንስትሩ አክለው እንዳስረዱት፡ የሞሪታንያ ክብር ዘብ በስህተት በፕሬዚደንታዊው የተሽከርካሪዎች አጀብ ላይ ተኩሶዋል። ይሁንና፡ አደጋውን በተመለከተ የተለያየ ታሪክ ስለሚሰማ የሆነውን በትክክል ማወቁ በወቅቱ አዳጋች መሆኑን ተያይዞ የደረሰን ዘገባ አስታውቋል። ቀደም ሲል አንድ ስማቸው ያልተገለጸ የጦር መኮንን በሰጡት መግለጫ ፕሬዚደንቱ በአንድ በሞተር ባይስክል ይጓዝ በነበረ ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ በሰሜናዊ ኑዋክሾት እንደተተኮሰባቸው አስታውቀዋል።

አርያም ተክሌ
ልደት አበበ