የምጣኔ ሃብት ምሁርና የጁዶው አሰልጣኝ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 18.09.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የምጣኔ ሃብት ምሁርና የጁዶው አሰልጣኝ

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እንደጨረሱ የነጻ ትምህርት እድል አግኝተው ምሥራቅ ጀርመን መጡ ። በምስራቅ ጀርመንዋ ስቪካው ከተማ የቋንቋ ትምህርት እንደደጨረሱም ትምህርት ጀመሩ ። ብዙም ሳይገፉ የበርሊኑ ግንብ መፍረስ ተማሪውን ፀጋዮን ስጋት ውስጥ ጣለ ።

ላለፉት 24 አመታት ጀርመን የኖሩት ዶክተር ፀጋዮ ደግነህ ተወልደው ያደጉት የመጀመሪያና የ 2 ተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉትም አዲስ አበባ ነው ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እንደጨረሱ የነጻ ትምህርት እድል አግኝተው ምሥራቅ ጀርመን መጡ ። በምስራቅ ጀርመንዋ ስቪካው ከተማ የቋንቋ ትምህርት እንደደጨረሱም ትምህርት ጀመሩ ። ብዙም ሳይገፉ የበርሊኑ ግንብ መፍረስ ተማሪውን ፀጋዮን ስጋት ውስጥ ጣለ ። ዶክተር ፀጋዮ በተማሪነት ዘመናቸው የበርሊኑ ግንብ ከፈረሰ በኋላ በምሥራቅ ጀርመን አፍቃሪ ናዚዎች በውጭ ዜጎች ላይ ይፈጽሟቸው የነበሩ ዘረኛ ጥቃቶችን ለመታዘብ በቅተዋል ። ርሳቸው ጥቃት ባይደርስባቸውም ከዘለፋ ግን አላመለጡም ። አሁንም ቢሆን በምሥራቅ ጀርመን ችግሩ አልተወገደምና ጥንቃቄ ተለይቷቸው አያውቅም ። በሥራው አለም ውስጥ ናቸው ።

Bahnstation Alexanderplatz in Berlin Aufnahmedatum: August 2011 Copyright: Kate Bowen / DW


ተማሪው ፀጋዮ ከስቪካው ወደ በርሊን ከመጡ በኋላም ከበርሊኑ ሁምቦልት ዩኒቨርስቲ በንግድ አስተዳደር የማስተርስ ዲግሪ ያዙ ። በዛው ዩኒቨርስቲ በረዳትነት ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ በኢኮኖሚክስ ወይም በምጣኔ ሃብት በተለይም የንብረት ባለቤትነት መብትን በመሳሰሉ የኤኮኖሚ ህጎችና በኢንቬስትመንት ላይ ባተኮረ የትምህርት ዘርፍ የዲክትሬት ዲግሪ ለመያዝ በቁ ። ከዚያን ጊዜ አንስቶ ዶክተር ፀጋዮ በሥራው አለም ውስጥ ናቸው ። የቤተሰብ ጉዳይ ከተነሳ ዶክተር ፀጋዮ የቤተሰብ ሃላፊ ናቸው
በጀርመን ኑሮን በቀላሉ ለመምራት እንደ ዶክተር ፀጋዮ ከህብረተሰቡ ጋር ተቀራርቦ ተዋህዶ መኖር አንዱ ብልሃት ነው ። በርሳቸው እምነት የውጭ ዜጎች በራሳቸው ከተማመኑ በጀርመናውያን ዘንድ ተቀባይነት ይኖራቸዋል ፤ ራሳቸውንም ማሳደግ ይችላሉ ። ለዚህም የራሳቸውን ተሞክሮ ነው በምሳሌነት የሚያቀርቡት ።
የምጣኔ ሃብት ምሁሩ ዶክተር ፀጋዮ ከመደበኛ ሥራቸው ውጭ በትርፍ ጊዜያቸው በሚያዘወትሩት የጅዶና ጁጁትሱ ስፖርትም ይታወቃሉ ። በዚሁ ስፖርት ጥቁር ቀበቶ ና ከዚያም ከፍ ላይ ደረጃ ያላቸው ዶክተር ፀጋዮ ሥልጠና ይሰጣሉ ፤ በፈታኝነትም ያገለግላሉ ። ኢትዮጵያም የዚህኑ ስፖርት ማህበር አቋቁመዋል ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic