የምግብ ዕጥረት በዚምባብዌ ዕስር ቤቶች
ረቡዕ፣ ሰኔ 3 2001ማስታወቂያ
በዕስር ቤቶች በምግብ ማጣት እና በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ያለቀውና የሚያልቀው ዕስረኛ ብዛት ጥቂት የሚባል አይደለም ። ይህን አሳዛኝ የዕስረኞች አያያዝ ለመለወጥ ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶችና በጎ ፈቃደኞች የበኩላቸውን ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው ። በዚህ ተግባር ከተሰማሩት ውስጥ አንዱ የዓለም ቀይ መስቀል ድርጅት ሲሆን የዚምባብዌ ታራሚዎችን ለመርዳት በግል የሚንቀሳቀሱ በጎ አድራጊዎችም አልጠፉም ። ከነዚህም መካከል ሐራሬ ውስጥ ባለፈው ዓርብ ለዕሰረኞቹ ዕርዳታ የሚውል የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ያካሄዱት ኢትዮጵያውያንና ጀርመናውያን ይገኙበታል ።
ሂሩት መለሰ/ሸዋዬ ለገሠ