የምግብ እጥረትና የጀርመን እቅድ | ዓለም | DW | 06.03.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የምግብ እጥረትና የጀርመን እቅድ

በአለም ደሐ ሐገሮች የሚታየዉን የምግብ እጥረት ለማቃለል ጀርመን የገጠር አካባቢዎችን ልማት የሚያፋጥን እቅድ ነድፋለች።

...አንጌላና ሽታይንማየር...

ሜርክልና ሽታይንማየር

የሐገሪቱ ምክር ቤት ትናንት በተነጋገረበት እቅድ መሠረት አብዛኛዉ የአፍሪቃ በጥቂቱ ደግሞ የእስያ ሐገራትን የገጠር ልማት ለማገዝ ጀርመን በአመት የስድስት መቶ ሚሊዮን ዩሮ ርዳታ ትሰጣለች።ይሕ የገንዘብ መጠን የጀርመን የልማት ተራድኦ ሚኒስቴር ከሚያወጣዉ አመታዊ በጀት አስር በመቶ ያሕል መሆኑ ነዉ።የሐሳቡ ደጋፊዎች እንደሚሉት እቅዱ ድሕነትንና ረሐብን ለመቀነስ፥ የለጋሽ ሐገሮችን አሰራርም ለመለወጥ ይረዳል።