የምግብ ርዳታ ፈላጊው ቁጥር ይጨምራል መባሉ | ኢትዮጵያ | DW | 08.12.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የምግብ ርዳታ ፈላጊው ቁጥር ይጨምራል መባሉ

በኢትዮጵያ እስከ ጥር ወር ድረስ የምግብ ርዳታ የሚስፈልገው ሕዝብ ቁጥር ከ10 ሚልዮን እንደሚበልጥ አሶሽየትድ ፕሬስ የኢትዮጵያን መንግሥት በመጥቀስ አስታወቀ። ከነዚሁ መካከል ስድስቱ ሚልዮን ህፃናት መሆናቸውንም ዘገባው አክሎ አስረድቶዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ አደጋ መከላከያ እና ዝግጁነት መስሪያ ቤት ኃላፊ አቶ ምትኩ ካሳ ትናንት እንደገለጹት፣ ለጋሽ ሃገራት ለመስጠት የገቡትን የምግብ ርዳታ ባለማቅረባቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ከራሱ፣ ለችግር ጊዜ ካከማቸው ምግብ በማከፋፈል ላይ ይገኛል። እንደ አቶ ምትኩ ገለጻ በድርቁ ሰበብ እስካሁን አንድም የሰው ሕይወት አልጠፋም። ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን እንደሚገምቱት፣ ድርቁ እስከ ጎርጎሪዮሳዊው 2016 ዓም ድረስ የሚቀጥል ሲሆን፣ የትራንስፖርት እና የምግብ አቅርቦት እጥረት ዓቢይ እንቅፋቶች ደቅነዋል። ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት ወዲህ በወቅቱ ከፍተኛ ድርቅ እንደገጠማት እና በዚሁ ሰበብ የተፈጠረውን ችግር ለመቋቋምም 1,4 ቢልዮን ዶላር ርዳታ እንደሚያስፈልጋት የግብረ ሰናዩ ድርጅት «ሴቭ ዘ ችልድረን» የኢትዮጵያ ቢሮ ኃላፊ ጆን ግራሀም አስታውቀዋል።

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ