የምግብ ርዳታ እና የጅቡቲ ወደብ | ኢትዮጵያ | DW | 22.02.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የምግብ ርዳታ እና የጅቡቲ ወደብ

የሰብዓዊ ርዳታ ለጋሾችና የኢትዮጲያ መንግሥት የምግብ ርዳታ ለሚፈልግ 10,2 ሚሊዮን ሕዝብ ምግብ ለማዳረስ ጥረት ላይ ይገኛሉ። በታህሳስ ወር የኢትዮጲያ መንግስት 1,5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንደማስፈልገዉ አሳዉቆ ነበር።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:21
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:21 ደቂቃ

ያልተቀላጠፈዉ ርዳታ ስርጭት በኢትዮጲያ

የምግብ ርዳታዉን ለማዳረስ አስቸጋሪ ከሆኑት ዉስጥ የጅቡቲ ወደብ ላይ የርዳታ እህልን ጭኖ የደረሱ መርከቦች ጭነታቸዉን ማራጋፍ ሳይችሉ ተጨናንቀዉ መቆማቸዉ ነዉ የተመለከተዉ። የኢትዮጵያን መንግሥት ጨምሮ ሌሎች የሰብዓዊ ርዳታ ድርጅቶች በጅቡቲ ወደብ የርዳታ ምግብ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ለማስገባት አንደ ዋነኛ በር ይጠቀሙበታል።በኢትዮጲያ የሚገኘዉ የዓለም የምግብ ርዳታ ድርጅት ቅርንጫፍ «WFP» ሥራ አስከያጅ ጆን አይሊፍ ለዶይቼ ቬሌ እንደተናገሩት በአሁኑ ሰዓት ወደ 20 የሚጠጉ መርከቦች የምግብ ርዳታን ጭነዉ ወደ ወደቡ ጉዞ ላይ ናቸዉ።
አሁን በጅቡቲ ወደብ ያለዉን የመርከቦች መጨናነቅ እና የርዳታ እህልን በተፈለገዉ መንገድ ለተረጂዎች አለማዳረስ አለመቻሉ ዋና መንስኤ ምን እንደሆነ በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲከስ አገልግሎት ድርጅት የዩኒሞዳል ኦፔሬሸን ኃላፊ የሆኑት እመቤት ሻዎል ወደብ አከባብ ዉጥረት መከሰቱን አብራርተዋል።

ወደብ አልባ የሆነች ኢትዮጲያ 70 በመቶ የሚሆነዉን ወደ አገር የሚገቡ ወይም የሚወጡ እንቅስቃሴዎችን በጅቡቲ ወደብ በኩል ነዉ የምታደርገዉ። በአገር ደረጃም ቢሆን የባህር ትራንስፖርቱን 12 በሚሆኑ መርከቦች ትጠቀማለች። ይሁን እንጂ ወደብ አከባቢ ያለዉን ችግር ለመፍታት መንግስት ስምንት ያህል ደረቅ ወደቦችን ገንብቶ እያንቀሳቀሰ ይገኛል።

የዓለም የምግብ ርዳታ ድርጅት ስራ አስከያጅ የሆኑት ጆን አይሊፍ እንደሚሉት ድርጅታቸዉ በርዳታ ለመስጠት ላቀደዉ ለ7,6 ሚሊዮን የምግብ ርዳታ እየደረሰ እንዳልሆነ ነዉ። ይህ ምግብ ርዳታ የታቀደዉ ሰዉን ለማዳን እናም ቀዉስ ለመቋቋም እንደሆነ ከተናገሩ በኋላ አገር ዉስጥ ካለዉ ገበያ ገዝቶ ማሟላት እንደማይችሉ አክለዉ ተናግሮዋል። እንደ ድርጅቱ ስራ አስከያጅ እንደ አይሊፍ በአሁኑ ሰዓት በወር 180,000 ቶን የምግብ ርዳታ ያስፈልጋል።

ባለፈዉ ታህሳስ ወር የኢትዮጲያ መንግስት 1,4 ቢልዮን ዶላር ርዳታን ለጋሽ አገሮችን ጠይቆ እንደነበር ይታወሳል። ይሁን እንጂ እንደ አቶ ምትኩ ካሳ ከተጠይቀዉ የርዳታ መጠን እስከ አሁን የደረሰዉ 46 በመቶዉ ብቻ እንደሆነ ለዶይቼ ቬሌ ተናግሮዋል።

መርጋ ዮናስ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic