«የምድር ነውጥ መንስዔ፣ በአፋር ስምጥ ሸለቆ፣» | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 17.02.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

«የምድር ነውጥ መንስዔ፣ በአፋር ስምጥ ሸለቆ፣»

ጥር 26 ቀን 2002 ዓ ም፣ በተሠራጨው ሳይንስና ኅብረተሰብ ዝግጅታችን፣ የምድር ነውጥ አዘውትሮ በሚጠናወተው የዩናይትድ እስቴትስ ምዕራባዊ ጠረፍ የሚኖሩትን፣ አሁን፣ በሳን ዲየጎ ዩኒቨርስቲ፣

default

የኢንጀሪንግ ፕሮፌሰር የሆኑትን ፤ ለዓመታት፣ ከህንጻ ምህንድስናና ከምድር ነውጥ ምርምር ጋር በተያያዘ ኢንጅኔሪግ፣ RAM ኢንተርናሽናል በተሰኘው ኩባንያ ውስጥ የአንድ ዘርፍ ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን የሠሩትን ዶ/ር ሳሙኤል ክንዴን፣ ከሄይቲው የምድር ነውጥ ድቀት ማግሥት፣ የምድር ነውጥ ሥጋት በኢትዮጵያ፣( Earthquake Risks in Ethiopia )በሚል ርእስ ፣ በድረ ገጾች ከተሠራጨ ጽሑፋቸው በመነሣት አነጋግረናቸው ነበር። በኢትዮጵያ ባለፉት ምዕተ-ዓመታት ገደማ፣ በተለያዩ ጊዜያት ያጋጠሙ የምድር ነውጦችን፣ የኃይላቸውን መጠንና ያደረሱትንም ጥፋት ፣ አውስተውልን እንደነበረ የሚታወስ ነው። ዶ/ር ሳሙኤል፣ በአፋር ስምጥ ሸለቆ ስለሚከሠተው የምድር ነውጥ መንስዔ ለሰጡት ማብራሪያ ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሥነ ምድር ሳይንስ የትምህርት ክፍል፣ ምርምሩ ፣ የተጠቀሰውን ማብራሪያ አያረጋግጥም ሲል በላከልን የፋክስ መልእክት ላይ አስታውቋል። ለአንዴትነቱ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ በሥነ ምድር የትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር ተስፋዬ ኪዳኔን አነጋግረናል። ዶ/ር ተስፋዬ ትምህርታቸው፣ በከርሠ-ምድር፣ የዐለት፣ መተጣጠፍን ፣ መሰባበርን ፣ የቋጥኝን ቅርጽና አቀማማጥ ፣ እንዲሁም የምድርን የመግነጢሳዊ ቀጣና ምርምር የሚዳስስ ነው።

(ድምፅ)-------------

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ