የምድር ነውጥን የሚቋቋሙ ህንፃዎች አሠራር ደንብ፣ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 03.02.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የምድር ነውጥን የሚቋቋሙ ህንፃዎች አሠራር ደንብ፣

ባለፈው ሳምንት በዚህ ክፍለ- ጊዜ፣ በሳን ዲዪጎ ዩኒቨርስቲ የኢንጅኔሪንግ ፕሮፌሰር ዶ/ር ሳሙኤል ክንዴ፣ ስለምድር ነውጥ ምንነት፣ ኢትዮጵያም ውስጥ፣ ባለፉት መቶ ዓመታት ገደማ ፣ ከተመዘገቡ ጥናቶች በመነሣት፣

default

በአጠቃላይም ፣ ከሥነ ምድር፣ እንዲሁም በከርሠ-ምድር ውስጥ ስለሚከሠት አርገብጋቢ የተፈጥሮ ኃይል ፣ ከአንጂኔሪንግ ጋር በማያያዝ ማብራሪያ የሰጡን መሆናቸው ይታወስ ይሆናል።

በዛሬው 2ኛ ና የመጨረሻ ክፍል ቅንብራችን ፣ የምድር ነውጥ አስከፊ ድቀት እንዳያደርስ በቤት ፣በመንገድ ፣ በድልድይና ግድብ ሥራ ረገድ ምን ዓይነት ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚበጅ ፣ አንድ የህንጻ መሃንዲስ አነጋግረናል። እርሳቸውም፣ በዚያው በሳንዲዪጎ ካሊፎርኒያ ፣ ዩናይትድ እስቴትስ ውስጥ የሚገኙት ኢንጂኔር ወይም የህንጻ መሃንዲስ አቶ ሳምሶን እንግዳ ናቸው። አቶ ሳምሶን በሲቭል ኢንጂኔሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪአቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ በፖሞና ፣ ከካሊፎርኒያ ፖሊቴክኒክ ዩኒቨርስቲም የማስተርስ ዲግሪአቸውን ያገኙ ሲሆን፣ በተጠቀሰው ፌደራል ክፍለ- ሀገር፣ የማጓጓዣ አገልግሎት ወይም የአውራ ጎዳና መሥሪያ ቤት ፣ የድልድይ ኢንጅኔር በመሆን 12 ዓመታት ከመሥራታቸውም ፣ በግንባታ፣ በንድፍና የምድር ነውጥ በሚያሠጋቸው አካባቢዎች፣ ድልድዮች ለየት ባለ ዘዴ እንዲሠሩ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ሲያደርጉ ቆይተዋል። በአሁኑ ጊዜ፣ በካሊፎርኒያና ሃዋይ የህንጻና ድልድይ ሥራ አማካሪ ከመሆናቸውም ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ፣ ቤቶች፣ ህንጻዎች፣ የተፈጥሮ አደጋን ለመከላከል በሚረዳ የአሠራር ደንብ እንዲገነቡ ካተኮሩት ፣ የምድርን አርገፍጋፊ ኃይል ፣ ግምት ውስ ጥ ካስገባው የኢትዮጵያ የኢንጀሪንግ የምክክር ኮሚቴ ፣ ከኢትዮጵያ የሲቭል ኢንጄኔሮች ማኅበርና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር ተባባሪ ናቸው። ለኢትዮጵያውያን ኢንጂኔሮች፣ ተማሪዎችና የህንጻ ተቋራጮችም ጠቃሚ ውይይት የሚካሄድበት ስብሰባ አዘጋጅተው እንደነበረ ታውቋል።

ኢትዮጵያውያን ፣ ምናልባት የጎርፍ ማጥለቅለቅ ወይም፣ ብርቱ ድርቅ ሲገባ ሊሆን ይችላል፣ የተፈጥሮ ቁጣም ሆነ መቅሠፍት እንዳጋጠመ የምናስበው።

የምድር ነውጥ፣ እምብዛም የምንጨንቅበት ጉዳይ አይመስልም። ይሁን እንጂ፣ አያድርስ እንጂ፣ ድንገት ቢያጋጥም፣ በሰውና ንብረት ላይ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ፣ በቅድሚያ በህንጽ ምህንድስና መርኅ መሠረት ፣ በታላላቅ ከተሞች፣ ቤቶች እንዴት ነው መሠራት ያለባቸው? ኢንጂኔር ሳምሶን እንግዳ--

(ድምፅ)------

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ