የምድር ነውጥና እሳተ-ገሞራ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 15.06.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የምድር ነውጥና እሳተ-ገሞራ

ባለፉት ጥቂት ቀናት ፣ በዓለም ዙሪያ በተለያዩ አካባቢዎች የምድር ነውጥና እሳተ ገሞራ መከሠታቸውን ልብ ብለን ይሆናል። በአፍሪቃው ቀንድም እንዲሁ! ምድራችን፤ የብሱና ውቅያኖሱ ቀዝቀዝ ይበል እንጂ፤ ውስጥ አካልዋ ግን ገና ያልበረደ የእሳት ሉል መሆኑ የታወቀ ነው።

default

ያም ሆኖ ፤ እሳተ ገሞራና የምድር ነውጥ ምንድን ነው ግንኑነታቸው?

በአፍሪቃው ቀንድ ፤ ከ 150 ዓመት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈነዳ እሳተ-ገሞራ፣ በህዝብ ዘንድ ያስከተለውን ድንጋጤ ያደረሰውንም መለስተኛ የበረራ አገልግሎት ሳንክ መነሻ በማድረግ በሳይንስና ኅብረተሰብ ቅንብራችን እንዳስሳለን ። ለጥንቅሩ ተክሌ የኋላ-

የምድራችን ቁጣ ከሰሞኑ አየል ያለ መስሏል። ከትናንት በስቲያ በምሥራቅ ኢንዶኔሺያ በሱላዌሲ ደሴት በሪሽተር መለኪያ፣ 6,9 ‚ በአሜሪካውያን ተመራማሪዎች ምዝገባ መሠረት 6,2 የደረሰ ኃይለኛ የምድር መንቀጥቀጥ አጋጥሞ ነበረ። በዚያው ዕለት፤ ከ 4 ወራት በፊት ክፉኛ የተጎዳችውን የኒውዚላንድ ከተማ ክራይስትቸርችን እንደገና አርገፍግፏት እንደነበረ ታውቋል። በቺሌ፤ ከፑየሁ ኮርዶን ኮዬ ተራራ ባለፈው ሰሞን የፈነዳ እሳተ ገሞራ፤ በአርጀንቲና ፣ ቺሌ፤ ዑሩጓይ እና ፓራጓይ የአየር በረራ እክል ፈጥሮ እንደነበረ አይዘነጋም። ጭሱ ከደቡብ አሜሪካ አልፎ፤ እስከኒውዚላንድና አውስትሬሊያ በበረራ አገልግሎት ላይ ችግር አስከትሎ ነበር።

ከሜክሲኮም ፖፖ ካቴ ፔትል ከተሰኘው ተራራ ከ 12 ቀን ገደማ በፊት እሳተ ገሞራ ፈንድቶ እንደነበረ የሚታወስ ነው። ይኸው በደቡብና ሰሜን አሜሪካ ፤ እንዲሁም በእስያ ከሰሞኑ በተመሳሳይ ወቅት የተከሠተ የምድር ነውጥ አፍሪቃንም ዳስሷል። አፋር ውስጥ በደንከል በረሃ፤ ኤርትራና ኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ባለፈው እሁድ ፤ እኩለ ሌሊት ገደማ ላይ ፤ ዱቢ ከተባለው ቦታ ምናልባትም ናብሮ ከተሰኘው ኮረብታ ፣ እሳተ ገሞራ ከመፈንዳቱ በፊት በዚያው ዕለት በተደጋጋሚ የምድር ነውጥ ማጋጠሙ፤ ከፍተኛውም በ ሪኽተር መለኪያ 5,7 ደርሶ እንደነበረ ተገልጿል። የምድር ነውጥና እሳተ ገሞራ ምን ዓይነት ግንኙነት ነው ያላቸው? በኢትዮጵያ የሥነ-ምድር ሳይንስ፤ የኅዋ ሳይንስና ሥነ ፈለክ ተቋም (Geophysics , Space Science and Astronomy)

መምህር፤ ተመራማሪና በአሁኑ ወቅት በተጨማሪ የተቋሙ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ሽመልስ ፍስሐ---

(ድምፅ) ------------- (3,29)

ባለፈው እሁድ ሌሊት በደንከል በረሃ የፈነዳው እሳተ ገሞራ፤ በስተምዕራብ 233 ኪሎሜትር ራቅ ብላ የምትገኘውን መቐለን ፣ ከተጠቀሰው እሳተ ገሞራ ከፈነዳበት ቦታ በስተሰሜን 350 ኪሎሜትር ራቅ ብላ የምትገኘውን አሥመራንም ማስደንገጡ አልቀረም። ሰኞ ጧት ለህዝቡ አስደንጋጭ ሆኖ ስለተገኘው ክሥተት በመቐለ የሳባ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ (ሼባ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ)የሥራ አመራር (ማንጅመንት ) መምህር ፣ አቶ መንገሻ ሀብቱ ከዚያ ዕለት አንስቶ እስከዛሬ ያለውን ሁኔታ፣ የዐይን ምሥክር እንደመሆናቸው መጠን እንዲህ ገልጸውልናል።

(ድምፅ)--------------------

ኢትዮጵያ የምድር ነውጥ የሚታወቅም የማይታወቅም በብዛት የሚከሥትባት አገር ናት። በሄይቲ አምና በጥር ብርቱ የምድር ነውጥ አደጋ ከደረሰ በኋላ ያነጋገርናቸው በካሊፎርኒያ ዩናይትድ እስቴትስ የሚኖሩት ዶ/ር ሳሙኤል ክንዴ ምን ብለውን እንደነበረ እናስታውሳችሁ።

የምድር ነውጥ አደጋ ሊያጋጥም በሚችላባቸው አካባቢዎች የሚኖር ህዝብ ታዲያ ምን ዓይነት ጥንቃቄ ነው ማድረግ የሚኖርበት ? በሌላ ጊዜ የምንመለስበት ጉዳይ ይሆናል ፤

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ