የምድር ባቡር ሠራተኞች ቅሬታ | ኢትዮጵያ | DW | 04.10.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የምድር ባቡር ሠራተኞች ቅሬታ

ምስራቅ ኢትዮጵያ ውስጥ የምድር ባቡር የቀን ሰራተኞች በቀን ክፍያ በደል ደርሶብናል እያሉ ነው። እነዚሁ በምዕራብ ሃራርጌ ዞን አሰቦት አካባቢ የሚገኙ የምድር ባቡር ሰራተኞች እንደሚሉት ሌላ ቦታ ለተመሳሳይ ስራ በቀን የሚከፈለው ከ50 እስከ 100 ብር ሲሆን እነሱ ግን 25 እና 30 ብር ብቻ እየተከፈላቸው ነው።

አንዳንድ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የምድር ባቡር ኩባኒያ የቀን ሰራተኖች ለዶቸቬሌ እንደገለጹት በእለት ክፍያ ኣከፋፈል ለያ በደል እየደረሰባቸው ነው። በሌላ ቦታ በተመሳሳይ የቀን ስራ ላይ የተሰማሩ የኩባኒያው ሰራተኖች እንደየ ስራ መደባቸው በቀን ከ50 እስከ 100 ብር ይከፈላቸዋል። እነሱ ግን ሰራተኖቹ እንደሚሉት ከ25 እስከ35 ብር ብቻ እየተከፈላቸው ነው። ይህንኑ ገልጸው ለአለቆቻቸው ቅሬታ ቢያቀርቡም ሰሚ ኣላገኙም ። እንዲያውም በዚሁ መሰረት የማትሰሩ ካልሆነ ከስራ ትባረራላችሁ የሚል ማስጠንቀቂያ ተሰቶናል ሲሉም ያማርራሉ። ጥያቄያቸውን ለሚመለከተው የኩባኒያው ወይንም የመንግስት አካል ኣቅርበው ለመሙዋገትም ኣቅሙም ሆነ እድሉም እንደሌላቸው የገለጹት እነዚሁ የምድር ባቡር ኩባኒያ የቀን ሰራተኞች የችግሩ መንስዔ ደግሞ ሌላ ምንም ነገር ሳይሆን ሙስና ነው ይላሉ።

CREC በመባል የሚታወቀውን የቻይና ተቁዋራጭ ኩባኒያ ለማነጋገር ያደረግነው ተደደጋጋሚ ሙከራ ኣልተሳካም። ይሁን እንጂ EREC ንም ሆነሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ኣካላት ለማነጋገር ጥረታችን ይቀጥላል።

ጃፈር አሊ

ሂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic