የምዕራብ ጎንደር ታጋቾች ተለቀቁ  | ኢትዮጵያ | DW | 25.02.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የምዕራብ ጎንደር ታጋቾች ተለቀቁ 

ባለፈው የካቲት 12 ቀን፣ 2011 ዓ.ም ከጎንደር ወደ ገንዳውሐ በመጓዝ ላይ የነበሩ መንገደኞች ትናንትና ሙሉ በሙሉ መለቀቃቸውን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሰዎቹ ትናንት ሙሉ በሙሉ ተለቅቀዋል፣ የድርጊቱን ፈፃሚዎችንም ለህግ ለማቅረብ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡


ባለፈው የካቲት 12 ቀን፣ 2011 ዓ.ም ከጎንደር ወደ ገንዳውሐ በመጓዝ ላይ የነበሩ መንገደኞች ትናንትና ሙሉ በሙሉ መለቀቃቸውን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዘለዓለም ልጅዓለም ዛሬ በክልሉ ወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት በጎንደር ዞን ገንዳ ውኃ ከተማ አካባቢ ታግተው የነበሩ ሰዎች ትናንት ሙሉ በሙሉ ተለቅቀዋል፣ የድርጊቱን ፈፃሚዎችንም ለህግ ለማቅረብ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ ኮሚሽነሩ አያይዘውም የመከላከያ ሰራዊትና የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች የጋራ ስምሪት ካደረጉበት ጊዜ ጀምሮ በምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች በፀጥታው ረገድ መልካም መሻሻሎች መታየቸውን ዘርዝረዋል፡፡ ሆኖም አሁንም ቢሆን በግለሰብና በቡድን የሚፈፀሙ የሰላም የማናጋት አዝማሚያዎች እንዳሉ ጠቁመው ይህንንም ማክሸፍ እንደተቻለ ነው አቶ ዘለዓለም በጋዜጣዊ መግለጫቸው የተናገሩት፡፡የክልልና የፌደራል የፀጥታ ኃይሎች ተግባብተው አይሰሩም፣ “በክልል የፀጥታ አመራሮች መካከል ልዩነቶች አሉ” እተባሉ የሚነዙ አሉባልታዎች መሰረት የሌላቸው ናቸው የሚሉት አቶ ዘለዓለም የፀጥታ ኃይሉም ሆነ ሕብረተሰቡ የአካባቢውን ሰላም ወደ ነበረበት ለመመለስ በጋራ እየሰሩ እንደሆነ ነው ያብራሩት፡፡መንግስት ከተፈቀደላቸው የፀጥታ ኃይሎች ውጭ የጦር መሳሪሪያ በጎንደር ከተማና ባካባቢው ይዞ መንቀሳቀስ ከከለከለ ወዲህ በአካባቢው የጥይት ድምፅ እንደማይሰማ የተናገሩት ኮሚሽነር ዘለዓለም አንዳንድ ወገኖች “የክልሉ መንግስት በጎንደር ከተማ ትጥቅ ሊያስፈታ ነው” እየተባለ የሚወራው ግን ፍፁም ሀሰት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዓለምነው መኮንን

 

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ