የምዕራብ ኦሮሚያ የጸጥታ ሁኔታ
ዓርብ፣ ሐምሌ 3 2012ማስታወቂያ
ከሁለት ቀናት በፊት በቄለም ወለጋ ዞን ሚኮ በተባለች ከተማ በሐጫሉ ሁንዴሳ ሞት ሐዘናቸውን ለመግለጽ አደባባይ የወጡ የአካባቢው ነዋሪዎች መንገድ በመዝጋታቸው ከጸጥታ አስከባሪዎች በተፈጠረ ግጭት የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል። ከድምፃዊው ግድያ በኋላ በምዕራብ ኢትዮጵያ በሚገኙት የኦሮሚያ ከተሞች የሰው ሕይወት ጠፍቷል፤ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውም አሉ። የዶይቼ ቬለው ነጋሳ ደሳለኝ በትናንትናው ዕለት የምሥራቅ ወለጋ የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ መታሰራቸውን ከፓርቲው አረጋግጧል። ነጋሳ በምዕራብ ኦሮሚያ ያለውን ሁኔታ ወደ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አስረድቶኛል።
ነጋሳ ደሳለኝ
አዜብ ታደሰ