የምዕራባዉያን ድብደባና ሊቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን | ኢትዮጵያ | DW | 23.03.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የምዕራባዉያን ድብደባና ሊቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን

የምዕራባዉኑ ጦር ድብደባ ከተጀመረ ወዲሕ ደግሞ ሁኔታዉ ከፍቷል። ብዙ ኢትዮጵያዉያን ከሥራ ተባረዋል።የሚበሉትና ለቤት ኪራይ የሚከፍሉትም የላቸዉም

default

ሊቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የምዕራባዉያን ሐገራት ጦር በሊቢያ ላይ የጀመረዉ ድብደባ ሕይወታቸዉን ላደጋ እንዳጋለጠዉ አስታወቁ።በስልክ ያነጋገርናቸዉ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች እንደሚሉት የሊቢያዉ ሕዝባዊ አመፅ ወደ እርስ በርስ ጦርነት ከተቀየረ ወዲሕ ብዙ ጓደኞቻቸዉ የደረሱበት አይታወቅም።የምዕራባዉኑ ጦር ድብደባ ከተጀመረ ወዲሕ ደግሞ ሁኔታዉ ከፍቷል። ብዙ ኢትዮጵያዉያን ከሥራ ተባረዋል።የሚበሉትና ለቤት ኪራይ የሚከፍሉትም የላቸዉም።የሐገሬዉ ሰዉ ያስፈራራቸዋል።ወደ ሌላ ሐገር መሰደድም አልቻሉም።ነጋሽ መሐመድ ሁለቱን የትሪፖሊ ነዋሪዎች አነጋግሯል።

ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ